የሲዳማ ከተሞች ከሆኑት ኣለታ ወንዶ፤ ዳሌ-ይርጋኣለም እና ከሃዋሳ በዘንድሮው ኣገር ኣቀፍ የከተሞች ውድድይ ምን ይጠበቃል? ዝግጅታቸው ምን ይመስላል? መረጃ ያላችሁ ሰዎች ተጋሩን። አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 24 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) አምስተኛው የከተሞች ሳምንት በ2006 ዓ.ም ከህዳር 11 አሰከ 17 በባህር ዳር ከተማ ሊከበር ነው። በአሉም "ከተሞቻችን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማእከላት በመሆን የመለስን ሌጋሲ ያስቀጥላሉ" በሚል መሪ ቃል ይከበራል። ለበአሉ አከባበር ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናቸውንም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስቴርና የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ዛሬ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። ለዚሁም በአሉ የሚመራበትን መሪ እቅድ ተዘጋጅቷል፤ ዝግጅቱን የሚያስተባብሩ የተለያዩ አደረጃጀቶችም በፌደራል፣ በክልሉ መንግስትና በከተማዋ አስተዳደር ደረጃ ተቋቁሟል። የበአሉ አላማም በከተሞች መካከለ ውድድርን መፍጠርና የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡትን በማበረታታት ለሌሎች ከተሞች አርአያ አንዲሆኑ ማድረግ ነው። ከ17 ሺ በላይ ህዝቦች ያሉዋቸው ከ150 በላይ ከተሞች በባአሉ ይሳተፋሉም ተብሎ ይጠበቃል። አራተኛው የከተሞች ሳምንት በያዝነው አመት 132 ከተሞችን በማሳተፍ በአዳማ ከተማ መከበሩ ይታወሳል። http://www.fanabc.com/index.php?option=com_content&view=article&id=5186:2013-08-30-08-26-30&catid=103:2012-08-02-12-34-36&Itemid=235
የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል