Skip to main content

Posts

Showing posts from July, 2013

ሲዳማን ጨምሮ ከደቡብ ክልል ዘንድሮ ከ83 ሺህ 100 ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ቀረበ

ሃዋሳ ሐምሌ 16/2005 በደቡብ ክልል በተጠናቀቀው የበጀት አመት 83 ሺህ 140 ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ ገለጸ፡፡ በቢሮው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መላኩ እንዳለ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ቡናው የቀረበው በክልሉ ቡና አምራች ከሆኑ የተለያዩ ዞኖች በሚገኙ 380 የህብረት ስራ ማህበራትና ከ330 በሚበልጡ የግል ባለሃብቶች እንዲሁም የቡና ተክል ልማት ድርጅት አማካኝነት ነው፡፡ በዘመኑ ለማዕከላዊ ገበያ ገበያ ከቀረበው ከዚሁ ቡና ውሰጥ 42 ሺህ 189 ቶን የታጠበና ቀሪው 40 ሺህ 951 ቶን ደግሞ ያልታጠበ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በስራው ላይም 394 የቡና ማዘጋጃ ኢንዱስትሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ ክንውኑ የእቅዱን 68 በመቶ መሸፉኑንና ከአምናው ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡ ከዕቅዱ ሊያንስ የቻለው ህገ ወጥ የቡና ግብይትና ዝውውር መበራካት እንዲሁም የአለም ገበያ ዋጋ መቀነስና መዋዥቅ ጋር ተያይዞ ቡና አምራቹ ገበሬና አቅራቢው ወደፊት ዋጋው ይጨምራል በሚል በክምችት መያዙ አቶ መላኩ በምክንያትነት ከጠቀሱት ውስጥ ይገኙበታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከክልል እስከ ቀበሌ በየደረጃው የተቋቋመው የቡና ጥራትና ንግድ ቁጥጥር አሰተባባሪ ግብረ ሀይል በማጠናከር ህገ ወጥ ንግድ እንዲቆም ለማድረግ በዘመኑ በተካሄደው እንቅሰቃሴ ጀንፈል፣ መርቡሽ፣ እሸት ቡና ጨምሮ ከ21 ሺህ 700 ኩንታል በላይ ቡና ከህገ ወጦች ተይዞ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ በህጋዊ መንገድ በመሸጥ ለመንግስት ገቢ መሆኑን የስራ ሂደቱ ባለቤቱ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ግምሩክ ባለስልጣን የሀዋሳ ቅርንጫፍ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ62 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የኮንትሮባንድ እቃ ያዘ

ሃዋሳ ሐምሌ 16/2005 በኢትዮጵያ ገቢዎችና ግምሩክ ባለስልጣን የሀዋሳ ቅርንጫፍ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ62 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የኮንትሮባንድ ዕቃ መያዙን አስታወቀ። የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ ፈቃደ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በአራት መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ክምችት ይገኝባቸዋል ተብሎ በተጠረጠሩ ከተሞች በተደረገ ፍተሻ 62 ሚሊዮን 400 ሺህ 986 ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ አዳዲስና ልባሽ ጨርቆች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ መድሀኒቶችና ሌሎች የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዘዋል። ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ውስጥ አዳዲስ አልባሳት፣ አሮጌ ልባሽ ጨርቅና ጫማ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ዘይትና ሌሎች ምግብ ነክ ምርቶች፣ መድሀኒቶች፣ ትምባሆና የትንባሆ ውጤቶች ከፍተኛውን መጠን የያዙ መሆናቸውን አቶ ያሬድ ገልጸዋል። በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ሲገባ የተያዘው የኮንትሮባንድ ዕቃ መጠን በገንዘብ ሲገመት ከ10 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው የተለያዩ ልባሽና አዳዲስ ጨርቆች መድሀኒቶችና የመዋቢያና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች መያዛቸውንና ኮንትሮባንድ የመያዝ አቅም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር እድገት ማሳየቱን ተናግረዋል። የኮንትሮባንድ ወንጀልን ለመቆጣጠር በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሚመራ ጥምር ኮሚቴ በክልል ደረጃና በክልሉ በሚገኙ አምስት ዞኖችና በምዕራብ አርሲ ዞንና በባሌ ዞን ደረጃ የፀረ ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ ከተዋቀረ ወዲህ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ መዳከሙን ገልጸዋል። በግማሽ ዓመቱ ኮንትሮባንድን በተመለከተ ለጽህፈት ቤቱ ከደረሱ ጥቆማዎች ውስጥ አብዛኞቹ ለውጤት መብቃታቸውንና በጥቆማዎቹ መሰረት በተሽከርካሪና በጋማ ከብት ተጭነው ወደ ሀ

ከሲዳማ ነጻ ኣውጭ ግንባር (ሲነግ) ተጠሪ ከሆኑት ከካላ ቤታና ሆጤሳ ጋር የወቅቱ የሲዳማ ፖለቲካ በተመለከተ የተደረገ ቃለ ምልልስ

New

ሲዳማን ጭምሮ በደቡብ ክልል መሬትን ሳያርሱ የማልማት ዘዴ የተሳተፉ አርሶ አደሮች ከፍተኛ ምርት ማግኘታቸውን አስታወቁ

አዋሳ ሐምሌ 15/2005 በደቡብ ክልል መሬትን ሳያርሱ የማልማት ዘዴ የተሳተፉ አርሶ አደሩች ከፍተኛ ምርት ማግኘታቸውን አስታወቁ፡፡ በአውስትራሊያ መንግስት ድጋፍ በወንዶ ገነት ግብርና ምርምር ተቋም የሀዋሳ መለስተኛ የበቆሎ ምርምር ማዕከል መሬትን ሳያርሱ የማልማት ምርምር ስራ እያካሄደ ነው። በክልሉ ሀድያ፣ ሲዳማና ጉራጌ ዞኖች በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች ከሁለት ዓመት በፊት በአምስት አርሶ አደሮች የተጀመረው መሬትን ሳያርሱ የማልማት የዕቀባ ግብርና በተያዘው ዓመት በ200 አርሶ አደሮች እየተከናወነ ይገኛል። ትናንት በምስራቅ ባድዋቾ ወረዳ ጨፋ 01 ቀበሌ በተከናወነ የመስክ ቀን ላይ ማሳቸው የተጎበኘላቸውና በምርምሩ የታቀፉ አርሶ አደሮች እንደገለጹት በግብርና ምርምር ተቋሙ በተደረገላቸው ድጋፍ መሬት ሳያርሱ በቆሎና ቦሎቄ በማልማት ቀደም ሲል ከሚያገኙት ምርት ብልጫ ያለው መሰብሰብ ችለዋል። አርሶ አደር ሞላ አመሌና እንደገለጹት በምርምሩ ታቅፈው መሬት ሳያርሱ በማልማታቸው ቀደም ሲል በሄክታር ሲያገኙ ከነበረው ምርት በ50 በመቶ ብልጫ ያለው ምርት ማግኘት እንደቻሉ ገልጸዋል። መሬት ሳያርሱ ለዘር የሚሆን መስመር በማዘጋጀት ብቻ የበቆሎና ቦሎቄ በማሰባጠር ዘርተው ቦሎቄ አንድ ዙር እንደሰበሰቡና በቆሎው እስኪደርስ ድረስ ሁለተኛ ዙር ቦሎቄ ዘርተው ቡቃያው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሌላው ወጣት አርሶ አደር ደግነት ደሳለኝ በበኩሉ እንዳለው ሳያርሱ በመዝራት ዘዴ አሰባጥሮ በማልማት የመሬቱን ለምነት መጠበቅ እንደሚቻል በተደረገው ምርምር ያገኘውን ዕውቀት መሰረት አድርጎ ወደ ልማቱ መግባቱንና በቆሎ ተሰብስቦ እስኪያልቅ በስሩ ቦሎቄ ሁለት ጊዜ በማምረት የቦሎቄ ዘር በማቅረብ ተጠቃሚ መሆን ችሏል። የቤተሰቡ የእርሻ ማሳ በከፍተኛ ደረጃ በጎርፍ የሚጠቃና ውሃ ይ

የአውሮፓ ኅብረት የፓርላማ ቡድን በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት አሳሳቢ ነው አለ

-    የቃሊቲን እስር ቤት እንዳይጎበኝ መከልከሉን ገለጸ  ለሦስት ቀናት በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረገው የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ የሰብዓዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ በአገሪቱ ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን አስታወቀ፡፡ ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በአስቸኳይ እንደፈቱም ጠይቋል፡፡ ከሐምሌ 8 እስከ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረገው የአውሮፓ ኅብረት የልዑካን ቡድን፣ በኢትዮጵያ የነበረውን ጉብኝት ካጠናቀቀ በኋላ ሰሞኑን በሒልተን ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነበር ይህንን የገለጸው፡፡  እንደ ቡድኑ ድምዳሜ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ዕንባ ጠባቂ ተቋም መቋቋማቸውና በቅርቡ የፀደቀው አገራዊ የሰብዓዊ መብት መርሐ ግብር የሚበረታታ ዕርምጃ መሆኑን ገልጾ፣ መንግሥት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ መሆኑን አስረድቷል፡፡  ከመንግሥትና ከተቃዋሚ ተወካዮች እንዲሁም ከሲቪል ማኅበረሰብ አካላት ጋር ሰፋ ያለ ምክክርና ውይይት ያደረገው ቡድኑ፣ በአገሪቱ ዲሞክራሲ ማበብ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ የሚተመንባቸው ነፃ ሚዲያና ሲቪክ ማኅበረሰባት በከፍተኛ ደረጃ እንዳይሠሩ የተደረጉ መሆናቸውን ገልጿል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ፀረ ሽብረተኝነት አዋጁን ጨምሮ የአገሪቱን የፖለቲካ ድባብ አፍነው ይዘውታል ያሉዋቸው ሕጎች እንዲከለሱ ቡድኑ መንግሥትን ጠይቋል፡፡ ለዚህም በእስር ላይ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትና ጋዜጠኞች ሐሳባቸውን በነፃነት የመግለጽ መብታቸውን በመጠቀማቸው ለእስር የተዳረጉ መሆናቸውን በመግለጽ፣ በአስቸኳይ እንዲፈቱ መንግሥትን ጠይቋል፡፡ እስረኞችን በመጎብኘት የመጀመርያ መረጃ ለማግኘት አቅዶ እንደነበረ ያስታወቀው ቡድኑ፣ ቃሊቲ እስር ቤትን እንዳይጎበኝና እስረኞችን

ሃዋሳን ጨምሮ “አንድነት” በህዝብ ጥያቄ በ16 ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍና ስብሰባ እጠራለሁ አለ

ባለፈው ሳምንት በጐንደርና በደሴ ሠላማዊ ሰልፍ ያካሄደው አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ፤ ተመሳሳይ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ ከበርካታ ከተሞች የህዝብ ጥያቄ እንደቀረበለት በመጥቀስ በ16 ከተሞች የተቃውሞ ሰልፉንና ህዝባዊ ስብሰባዎች ለማካሄድ እንደወሰነ ገለፁ፡፡ በአዲስ አበባ ሐምሌ 28 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ታቅዶ እንደነበር የተናገሩት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ዳንኤል ተፈራ፣ ከጐንደርና ከደሴ የተቃውሞ ሰልፍ ጋር ተመሳሳይ ሰልፍ ለማካሄድ ከተለያዩ የኦሮሚያና የደቡብ አካባቢዎች ተደጋጋሚ የህዝብ ጥያቄ ስለቀረበለት ፓርቲው አዲስ ፕሮግራም ለማውጣት እንደወሰነ ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባውን ለማዘግየትና መስከረም 5 ቀን 2006 ለማድረግ እንደታሰበ ነግረውናል፡፡ በደቡብ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በአማራ፣ በቤንሻንጉል፣ በጋምቤላ እና በሀረሪ ክልሎች ተከታታይ ሠላማዊ ሠልፎችና የአደባባይ ስብሰባዎችን ለማካሄድ ፓርቲው ወስኗል ያሉት አቶ ዳንኤል፤ የአዲስ አበባው ሰላማዊ ሰልፍ ወደ መስከረም ተራዝሟል ብለዋል፡፡ ይሁንና ፓርቲው በአዲስ አበባ በቀጣዮቹ ሦስት ሳምንታት የአደባባይ ወይም የአዳራሽ ስብሰባዎችን ይጠራል ተብሏል፡፡ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ሐሙስ እለት ተወያይቶ መርሃግብር እንዳዘጋጀ አቶ ዳንኤል ጠቅሰው፤ በ16 ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ህዝባዊ ስብሰባ የሚካሄደው ከሐምሌ 28 ጀምሮ ነው ተብሏል፡፡ በጂንካ፣ በአርባ ምንጭና በባህርዳር ሠላማዊ ሰልፍ በሚካሄድበት በዚሁ እለት፣ በወላይታና በመቀሌ የአደባባይ ስብሰባ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል፡፡ ነሐሴ 12 ቀን፣ በወሊሶ፣ በናዝሬት፣ በፍቼ እና በባሌ ሠላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ አቶ ዳንኤል ጠቅሰው፤ ነሐሴ 26 በድሬዳዋ እና በጋምቤላ የአደባባይ ስብሰባ እንዲሁም በአሶሳ ሰላማ

ሕዝብ ‹‹ችግር ፈቺ አካልን ያየህ ወዲህ በለኝ›› እያለ ነው!

በተደጋጋሚ እንደምንገልጸው በአሁኑ ጊዜ መንግሥት የሙስና ወንጀልን ለመከላከልና ሙሰኞችን ለመቅጣት አዎንታዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ መቋጫው ለፍርድ ቤት የሚተው ቢሆንም ጅምሩ የሚያበረታታ ነው፡፡ ብቃት የላቸውም፣ ሌላ ሥራ ቢሠሩ ወይም ሌላ ኃላፊነት ቢሰጣቸው ይሻላል ተብለው የሚነሱትንና የሚዛወሩትንም እያስተዋልን ነን፡፡ እንቅስቃሴው የሚመዘነው በውጤቱ ቢሆንም ደፈርና ፈጠን ብሎ ዕርምጃ ለመውሰድ መራመዱ ራሱ በአዎንታ የሚታይ ነው፡፡   ይህንን የመንግሥት እንቅስቃሴ በትኩረት እየተከታተለ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ከእንቅስቃሴው ጋር በተያያዘ ለመንግሥት አንድ ግልጽና ግልጽ የሆነ ጥያቄ እየቀረበ ነው፡፡ ‹‹እነዚህ ሙሰኞች፣ ወንጀለኞች፣ ብቃት የለሽ ሹሞች በሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ የፈጸሙብኝ በደል መፍትሔ ያገኛል ወይ?›› የሚል ግልጽ ጥያቄ ነወ፡፡ ሙሰኞችም፣ አቅመ ቢሶችም፣ አስመሳዮችም፣ ፀረ ሕዝቦችም ሌሎች ሌሎች ወንጀለኞችም ሥራቸውን በሚገባ አልሠሩም ሲባል ትርጉሙ ግልጽ ነው፡፡ ሕግ ጥሰዋል፣ የሕዝብ ጥያቄ አልመለሱም፣ የሕዝብ ቅሬታ አልተቀበሉም፣ በሕዝብ የተሰጣቸውን ኃላፊነት አልተወጡም ማለት ነው፡፡ ይህ ማለትም በእነሱ ምክንያት ሕዝብ በደል ደርሶበታል ማለት ነው፡፡   በመሆኑም እነሱ ከሥልጣናቸው ሲነሱ፣ ሲታሰሩና ሲጠየቁ ለመሆኑ የፈጸሙት ምንድነው? ያደረሱት በደል ምንና ምን ያህል ነው ተብሎ ይመረመራል? የፈጠሩትን ችግር የሚፈታ ዕርምጃ ይወሰዳል? ወይስ እነሱ ይነሳሉ፣ በደልም ይረሳል፣ ሰሚ እንዳጣ ይቀጥላል ማለት ነው? መንግሥት እየወሰደው ካለው ዕርምጃ ጎን ለጎን ‹‹ችግር ፈቺ አካል›› ማቋቋም አለበት፡፡ ችግርና አቤቱታ እየመረመረ መፍትሔ የሚሰጥ ቡድን ወይም አካል ሊያቋቋም ይገባል፡፡ አለበለዚያ ‹‹ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም

በቅርቡ በምካሄደው የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ጉባኤ ላይ የዞኑ ካቢኔ ሽግሽግ እንደምኖር ተሰማ

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለወራንቻ ኢፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናገሩት የሲዳማ ዞን ኣሰተዳደር ኣቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በሃዋሳ ከተማ ከንቲባ በኣቶ ዮናስ ዮሰፍ ይተካሉ ተብሏል። በኣቶ ዮናስ ቦታ የሃዋሳ ከተማ ኣዲስ ከንቲባ የምሾምላት ሲሆን የወቅቱ የከተማዋ ትምህርት መምሪያ ሃላፊ ኣቶ ቃሬ የከተማዋ ከንቲባ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን 

ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም በደቡብ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ መደበኛ ጉባዔ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው የተመረጡት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አቶ ደሴ ዳልኬ ሥራቸውን በይፋ ጀመሩ

የሲዳማ ብሔር ተወላጅ የሆኑት አቶ ደሴ በቅርቡ የትምህርት ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙት ከቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ላይ የክልሉን መንግሥት ኃላፊነት ተረክበዋል፡፡ አቶ ደሴ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ማዕከል የሆነውን የደቡብ ክልል ኃላፊነት ሲረከቡ እንደተናገሩት፣ ለሕዝቡ እኩል የልማት ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ የክልሉን ሕዝብ አንድነት ለማጠናከርና የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ እንደሚሠራ አስታውቀዋል፡፡ አዲሱ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ምንም እንኳን በክልሉ ሴክተር መሥርያ ቤቶች ከዚህ ቀደም ባይሠሩም፣ ከ1996 ዓ.ም እስከ 1998 ዓ.ም የይርጋ ዓለም ከተማ ከንቲባ፣ ከ1998 ዓ.ም እስከ 2000 ዓ.ም የሲዳማ ዞን ትምህርት መምርያ ኃላፊ፣ ከ2000 ዓ.ም እስከ 2003 ዓ.ም የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ማገልገላቸው ታውቋል፡፡ ከ2003 ዓ.ም እስከ 2005 ዓ.ም ሰኔ ወር ድረስ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በመሆን የሠሩ ሲሆን፣ ከሐምሌ 6 ቀን ጀምሮ አዲሱን ኃላፊነታቸውን ተረክበዋል፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ፋኩልቲ በባይሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን፣ ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በለውጥ አመራር ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙት አቶ ደሴ፣ በአዲሱ ሹመት የተሻለ ለውጥ ያስመዘግባሉ ተብሎ እምነት ተጥሎባቸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በዞን ደረጃም ሆነ በፌደራል ደረጃ የነበራቸው የሥራ አፈጻጸም ለዚህ ኃላፊነት እንዳበቃቸው በክልሉ ምክር ቤት ጉባዔ ላይ ከተሳታፉ ግለሰቦች አስተያየት ለመረዳት ተችሏል፡፡ “አቶ ደሴ በተለይ በሲዳማ ዞን አስተዳዳሪነታቸው ወቅት ባሳዩት አመራር የተነሳ ክልሉን በፍትሐዊነት ያስተዳድራሉ ተብሎ ይጠበቃል፤” ሲሉ አንድ የክልሉ ባለሥልጣን ለሪፖር

በሲዳማ ዞን ከ186ሺህ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት የክረምት የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም በይፋ ተጀመረ፡፡

photo http://www.flickr.com/photos/espsol/sets/72157632677473483/ አዋሳ ሐምሌ 11/2005 በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ከ186ሺህ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ትናንት ተጀመረ ። የወጣቶችን የስራ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት እንዲጠናከር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የክልሉ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የፕሮግራሙ መጀመር ምክንያት በማድረግ በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ ትናንት በተዘጋጀው መድረክ ላይ የዞኑ ሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃለፊ ውይዜሮ ሻሎ ሮርሳ እንደገለጹት የዞኑ ወጣቶች ባለፉት አራት ዓመታት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተደራጀ መንገድ በመሰማራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባሮችን ሲያከናዉኑ ቆይተዋል ። የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን ወጣቶቹ ጉልበታቸውን፣ እውቀታቸውን ለአካባቢው ልማት በማዋል መልካም ተግባሮችን ከማከናወናቸዉም ሌላ ከማህበረሰቡ የተለያዩ እሴቶችን የቀስሙበት እንደነበር አስታዉቀዋል ። በዘንድሮም ክረምት ከዞኑ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ከወጣት አደረጃጀቶች ጋር በመተባበር እራሳቸውንና ህብረተሰቡን ጠቅመው የዞኑን ልማት በሚያፋጥኑ የልማት ተግባሮች ለመሰማራት እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ወይዜሮ ሻሎ አብራርቷል፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አክልሉ አዱሎ በበኩላቸው የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ በከተማው ከተጀመረ ወዲህ ወጣቶች ለልማት ያላቸዉ ተነሳሽነትና ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል ብለዋል፡፡ ወጣቶቹ በቆይታቸዉ የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት ፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የጤና፣ የአካባቢ ፅዳትና ውበት፣ የትራፊክ ደህንነት፣ አረጋውያንና

ኣገሬ ሰላም እኣኣ በ1963 እስከ 1967 ከ60 ኣመት በፊት በፎቶ

ተጨማሪ ፎቶ ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ

Hawassa University graduation ceremony Main Campus(Photos )

Hawassa University graduation ceremony Main Campus take a look at photos

በሀዋሳ ከተማ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች ፈቃድ ተሰጠ

አዋሳ ሐምሌ 10/2005 በሀዋሳ ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ523 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 56 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ ለመግባት እየተዘጋጁ መሆናቸውን የከተማው ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ገለጸ፡፡ በከተማው የዘንድሮን ሳይጨምር 5 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያላቸው ሌሎች ባለሀብቶች በፈጠሯቸው የስራ እድሎች ከ28ሺህ 600 ለሚበልጡ ዜጎች ተጠቃሚ ማድረጋቸውም ተገልጿል፡፡ በመምሪያው የኢንቨስትመንት ፍቃድ መስጠት ፐርፎርመርና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ወግደረስ ወንድሙ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በተጠናቀቀው የበጀት አመት ከ523 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል በማስመዝገብ ፍቃድ የወሰዱት 56 ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፣ በኮንስትራከሽን ፣በሆቴልና ሌሎች ማህበራዊ አገልገሎቶች ለመሰማራት ነው፡፡ ባለሀብቶቹ በግላቸው ባላቸውና በጊዜዊነት በተሰጣቸው ቦታዎች በአሁኑ ወቅት ወደ ስራ ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆናቸውና ስራ የጀመሩ እንዳሉ አመልክተው በሙሉ አቅማቸው ሲንቀሳቀሱ 2ሺህ ሰዎች የስራ እድል ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለኢንቨስትመንት ልማት የሚውል 420 ሄክታር የሚጠጋ መሬት ዘንድሮ በጥናት ተለይቶ ለአልሚ ባለሀብቶች መዘጋጀቱንና ከዚሀም ውስጥ 270 ሄክታር በሀገር አቅፍ ደረጃ በማዕከላዊ መንግስት ለአንዱስትሪ ልማት የሚፈለግ ነው ብለዋል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለኢንዱስትሪ ልማት ከተመረጡ አምስት ከተሞች መካከል ሀዋሳ አንዷ በመሆኗ ማዕከላዊ መንግስት ከውጪና ከሀገር ውስጥ ለሚጋብዛቸው አልሚ ባለሃብቶች እንዲውል ያዘጋጁት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ቀሪው 150 ሄክታር መሬት በኢንዱስትሪ፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣በሪል ስቴትና በአገልግሎት ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብ

ሃዋሳን ጨምሮ የከተሞች ማስፋፍያ እና የኢኮኖሚ እድገት መርሀ ግብር ተግባራዊ ሊሆን ነው

የከተሞች የተቀናጀ ማስፋፍያ እና የልማት መርሀ ግብርን ተግባራዊ ማድረግ በከተሞች አያደገ ለመጣው የመሬት አቅርቦት ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ እንደሚሰጥ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የከተሞች ማስፋፍያ እና አካባቢ ልማት መርሀ ግብር ማስጀመሪያ ወርክሾፕ እየተካሄደ ነው፡፡ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር አቶ ሞክርያ ሀይሌ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በከተሞች መሰረተ ልማት፣ እድገት እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትኩረት ያደረገ ስትራቴጂ ተግባራዊ ተደርጎ በከተሞቹ የማስፈፀም አቅምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ውጤት የተገኘ ቢሆንም የተቀናጀ የከተሞች ማስፋፋትና የልማት ፕሮግራምን ውጤታማ ከማድረግ አንፃር ግን ብዙ መስራት ይጠበቃል ብለዋል፡፡ አሁን በኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ አድራጊነት በሙከራ ደረጃ በአራት ከተሞች ላይ ተግባራዊ የሚደረገው የከተሞች ማስፋፊያ እና አከባቢ ልማት መርሀ ግብር ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚያግዝም ጠቁመዋል፡፡ መርሀ ግብሩ በፈጣን የከተሞች መስፋፋት እና የኢኮኖሚ እድገት ሳቢያ እያደገ ለመጣው የቤቶችና ኢንዱስትሪ ግንባታዎች የመሬት አቅርቦት እንዲኖር ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር ባለፈ የከተሞችን ገቢ በማሳደግ ረገድም ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡ መርሀ ግብሩ በሙከራ ደረጃ በአዳማ፣ ሀዋሳ፣ ባሀርዳር እና መቀሌ ከተሞች ላይ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን በመጪው ጥር ወር ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ፅሕፈት ቤት ዘግቧል፡፡ http://www.ertagov.com

ሰለ ሲዳማ ቡና

Ethiopian Distinct Coffee  Sidamma The region of Sidama is in southern Ethiopia. It encompasses many individual origins, including, geographically, the area of Yirgacheffe. However, Yirgacheffe is classified as its own separate origin. In this section, we discuss Sidama as a designated coffee origin. The name Sidama is often spelled "Sidamo," and the two names are generally used interchangeably. Some of the confusion comes from earlier political designations that called Sidama the large federal region which stretches from the town of Shashemene in the north all the way to the Kenyan border; and which called Sidama a much smaller sub-region which contains the towns of Hawassa (Awassa), Yirga Alem, and Dila. All the coffee origins designated as Sidama are within the larger territory of Sidama, but not all are within the smaller state of Sidama. To avoid confusion, it's best to just consider all the central-southern Ethiopian coffees as Sidama, and then use the spe

ዩኒቨርስቲው 26 አዳዲስ ፕሮግራሞችን ለመክፈት እየሰራ ነው

ሃዋሳ ሐምሌ 8/2005 በድህረና ቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ለ26 አዲስ ፕሮግራሞች ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ገለጹ፡፡ በዩኒቨርስቲው የሀዋሳ ግብርና፣ ህከምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያየ ሙያ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ መርሀ ግብር ያሰለጠኗቸውን ከ900 የሚበልጡ ተማሪዎች ትናንት አስመርቀዋል፡፡ የዩኒቨርሰቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሴፍ ማሞ እንደገለጹት በተጠናቀቀው የትምሀርት ዘመን ለ18 አዳዲስ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ስርዓተ ትምህርት ቀረጻ ተጠናቆ አንዳንዶቹ ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር እንቅስቃሴ ጀምረዋል፡፡ ከፕሮግራሞቹ መካከል አግሪ ቢዝነስና ቫሊዩ ቼን ማኔጅመንት፣ በባዮቴክኖሎጂ ፣በአግሮ ኢኮሎጂና ሰስቴነብል አግሪካልቸር ይገኙበታል፡፡ በህክምና ትምህርት ቤት ደግሞ በውሰጥ ደዌ፣ በሀጻናት ህክምና፣ በቀዶ ጥገና ፣ በማህጸን ጽንስ ስፔሻሊቲ የስልጠና ፕሮግራም ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ለመክፈት ዝግጅት መደረጉ ተመልክቷል፡፡ በቅድመ ምረቃ በቅርቡ ከተከፈተው የሲዳምኛ ቋንቋ በተጨማሪ ለ7 ፕሮግራሞች ስርዓተ ትምህርት ተቀርጾ በአንዳንዶቹ ተማሪዎችን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ዶክተር ዮሴፍ ጠቁመዋል፡፡ ይህም ዩኒቨርስቲው የቅበላ አቅሙን በመደበኛ ፕሮግራም ብቻ አሁን ያሉትን 17 ሺህ 080 ተማሪዎችን ቁጥር በ2007 ወደ 26 ሺህ ለማድረስ የተያዘው ፕሮግራም አንዱ አካል በመሆኑ ለዚህ ስኬት ከማስፋፊያ ግንባታዎች ባሸገር ቀልጣፋና ዘመናዊ አሰራር መዘርጋታቸውን ገልጠዋል፡፡ የመምህራንን አቅም በማጎልበት ረገድ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ከ400 በላይ መምህራን በሀገር ውስጥና በውጪ የከፍተኛ ትምህርታቸውን እየተማሩ ይገኛል ብለዋል፡፡ በመንግስት የተጀመረው የልማት እንቅስቃሴ በጥናትና ምር

የደቡብ ክልል ምክር ቤት 7ኛ መደበኛ ጉባኤ ከ15 ነጥብ 4ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አፀደቀ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 07/2005 (ዋኢማ) - የደቡብ ክልል ምክር ቤት 7ኛ መደበኛ ጉባኤ ዘንድሮ በክልሉ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች ማስፈፀሚያ ከ15 ነጥብ 4ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አፀደቀ ፡፡  ምክር ቤቱ ያፀደቀው በጀትም ከቀዳሚው ዓመት ከ1 ቢሊዮን 480 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለውም ተገልጿል፡፡  የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለብርሃን ዜና በጀቱን ለክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ አቅርበው ባጸደቁበት ጊዜ እንደተናገሩት በጀቱ ለመሰረተ ልማት ፣ ለድህነት ተኮር ፕሮግራሞች፣ ለምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦችና ለመልካም አስተዳደር ስራዎች ማስፈጸሚያ ይውላል፡፡  ለክልሉ ከተመደበዉ በጀቱ ዉስጥ ከ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር የሚበልጠው ከፌዴራል መንግስት የቀመር ጥቅል ድርሻ፣ ከ3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ከክልሉ ከተለያዩ የገቢ ምንጮች የሚሰበሰብ ሲሆን ከ3 ቢሊዮን 015 ሚሊዮን ብር በላይ ደግሞ ለምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያ ከፌዴራል መንግስት ድጋፍ የሚገኝ ነዉ ።  እንዲሁም ከውጭ ሀገራት ይገኛል ተብሎ ከሚጠበቀው ገንዘብ 6 ሚሊዮን 882 ሺህ ብር በብድር ፣ 116 ሚሊዮን 842 ሺህ ብር ከእርዳታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡  አጠቃላይ ከተመደበው በጀት ውስጥም ለታችኛው የአስተዳደር እርከን በዓላማ የተገደበ በጀት 76 በመቶ ሲሆን ቀሪው 24 በመቶ ለክልሉ ቢሮዎች የተያዘ መሆኑን አቶ ኃይለብርሃን ገልፀዋል፡፡ የበጀት ክፍፍል ሲደረግ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና ልማት ስራዎች፣ መስኖና የንጹህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታ፣ እንዲሁም የአስተዳደርና ሌሎች ሴክተሮች ወጪ በጥልቀት እንዲካተት መደረጉን አስታውቀዋል፡፡  የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ዴሴ ዳልኬ በሰጡት አስተያየትም የክልሉ በጀት የተደለደለዉ ህገ መንግስቱን መሰረት በማድረግ በፍ

በክልሉ የተጀመሩ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል፡፡ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የተጀመሩ የልማት፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ሰርዓት ግንባታ ለማጠናከር ትኩረት ይሰጣል

አዋሳ ሐምሌ 07/2005 በደቡብ ክልል የተጀመሩ የልማት፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ሰርዓት ግንባታ በማጠናከር ፍትሃዊ የልማት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አዲሱ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለጹ፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ መንግስት የ2006 በበጀት ዓመት እቅድ ለምክር ቤቱ አባላት አቅርበዋል፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ባለፉት ሶስት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በየዘርፉ ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር በመገምገምና መልካም ተሞክሮዎችን በመለየት በቀጣይ በሁሉም የልማት መስኮች ውጤታማ ስራዎችን ለማከናወንና የህብረተሰቡን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ርብርብ ይደረጋል፡፡ በርብርቡ የሚካሄደው መንግስትና በድርጅት የቅርብ አመራር ሰጭነት፣ በባለሙያው ድጋፍና ክትትል እንዲሁም በህብረተሰቡ የተሟላ ተሳትፈፎና በቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም በየስራ ዘርፉ የግንባር ቀደም ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋት በገጠርም ሆነ በከተማ ድህነትን ለማስወገድ በሚያስችል መልኩ የጋራ ጥረት እንደሚደረግ አመልክተዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት በክልሉ ታቅደው ላልተከናወኑ ተግባራት በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር፣ የአስፈፃሚውና የፈፃሚው አቅም ውስንነት፣ቴክኖሎጂውን በተሟላ ሁኔታ ያለመጠቀም በዋናነት እንደሚጠቀሱ ተናግረዋል፡፡ እነዚህን ጉድለቶችን ለመቅረፍ የመንግስት፣ የድርጅትና የዝህብ ክንፎችን አቅም አቀናጅቶ በየደረጃው የልማት ሰራዊት በመገንባት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና የሚሌኒየም የልማት ግቦችን ለማሳካት የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚከናወኑ ገልፀዋል፡፡ በግብርናው መስክ አርሶአደሩ የተሻሻሉ ቴክኖሎጅዎችን ተጠቅሞ ምርትና ምር

ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት መምህራን የፕሮፌሰርነት ማእርግ ሰጠ

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 4ሺህ723 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለ14 ጊዜ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 723  ተማሪዎች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ አስመርቋል፡፡ከተመራቂዎች ውስጥ 556ቱ  በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው፡፡ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት መምህራን ንጋቱ ረጋሳ እና ተስፋየ ሲመና   የፕሮፌሰርነት ማእርግ ሰጥቷል፡፡ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ 1ሺህ 352 ተማሪዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ  ሀምሌ 6/2005 ዓ/ም አስመርቋል፡፡ከተመራቂዎች በመጀመሪያ ዲግሪ 489 ወንዶችና 182 ሴቶች፣ በሁለተኛ ዲግሪ 515 ወንዶችና 166 ሴቶች ናቸው፡፡ http://www.ertagov.com/amharic/index.php/component/k2/item/1342-%E1%88%83%E1%8B%8B%E1%88%B3-%E1%8B%A9%E1%8A%92%E1%89%A8%E1%88%AD%E1%88%B2%E1%89%B2-%E1%88%88%E1%88%81%E1%88%88%E1%89%B5-%E1%88%98%E1%88%9D%E1%88%85%E1%88%AB%E1%8A%95-%E1%8B%A8%E1%8D%95%E1%88%AE%E1%8D%8C%E1%88%B0%E1%88%AD%E1%8A%90%E1%89%B5-%E1%88%9B%E1%8A%A5%E1%88%AD%E1%8C%8D-%E1%88%B0%E1%8C%A0

የኢሜግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች ዋና መምሪያ አዋሳ በሚገኘው ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ ከህገ ወጥ ደላሎች ጋር በመመሳጠር ተገልጋዮችን አንገላተዋል ያላቸውን 11 ሰራተኞች በህግ ቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6 ፣ 2005 (ኤፍ.ቢ. ሲ) የኢሜግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች ዋና መምሪያ በስራዬ ላይ እንቅፋት ሆነዋል ባላቸው የተቋሙ ሰራተኞችና ህገወጥ ደላሎች ላይ ከሚመለከታቸው አካለት ጋር በመሆን በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አደረገ፡፡ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረጉት ተቋሙ አዋሳ በሚገኘው ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ ከህገ ወጥ ደላሎች ጋር በመመሳጠር ተገልጋዮችን አንገላተዋል ያላቸውን አስራ አንድ ሰራተኞቹ ፡፡ የኢሚግሬሽን ዜግነት ጉዳዮች ዋና መምሪያ የሚሰጠው አገልግሎት ፈጣንና ቀልጣፋ አይደለም በዚህም ለእንግልት እየተዳረግን ነው የሚሉና መሰል አቤቱታዎች በተገልጋዩ ዘንድ የሚነሱ ቅሬታዎች ናቸው፡፡ ተቋሙ የችግሩ መንስኤዎች የህግ ወጥ የደላሎች መበራከትና አሁን ካለው የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር ተያይዞ የመጣ መሆኑን በመግለፅ  ፤ ለዚህም ያካሄድኳቸው ግምገማዎችና ክትትሎች ማሳያ ናቸው ብሏል፡ የዋና መምሪው ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ሀይለ ጊዮርጊስ እንደሚሉት ፥ አዲስ አበባ በሚገኘው ዋናው ተቋም የሚስተዋለው የአገልግሎት መጨናነቅ ህገወጥ ደላሎች ለፓስፖርት ፈላጊዎች በሚሰጡት የተሳሳተ መረጃ ምክንያት የተከሰተ ነው ብለዋል፡፡ “በክልሎች ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጡ  ስድስት መስሪያ ቤቶች ቢኖሩም ህገወጥ ደላሎቹ ተጨማሪ ብር ለማግኘት ትክክለኛው ፓስፖርት ያለው አዲስ አበባ ነው በማለትና ተገልጋዩን ቪዛ እናመጣላችዋለን እያሉ  ፓስፖርታቸውን እየቀሙ ይወስዳሉ " ብለዋል፡፡ በህገወጥ ደላሎችና በአንዳንድ የተቋሙ ሰራተኛች መካከል ተፈጥሮ የነበረው የጥቅም ትስስርም ሌላኛው የችግሩ መንስኤ መሆኑን ነው አቶ ጌታቸው ያስረዱት፡፡ ህገወጥ ደላሎቹ ከሰራተኛቹ ጋር በመመሳጠር ባለጉዳዮች ገንዘብ ከከፈሉ ፓስፖርት የሚወሰድበ

በደቡብ ክልል በተጠነቀቀው በጀት ዓመት በሁሉም የልማት መስኮች የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል

አዋሳ ሐምሌ 06/2005 በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሁሉም የልማት መስኮች መላውን የክልሉን ነዋሪ ተጠቃሚ ያደረጉ አበረታታች ስራዎች መከናወናቸውን የትምህርት ሚኒስትር በመሆን የተሾሙት የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ። ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለክልሉ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ መደበኛ ጉባኤ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ እንዳሉት በተጠናቀቀው በጀት አመት በግብርና በትምህርት በጤና በመንገድ በንግድ ኢንዱስትሪ፣በከተማ ልማትና ሌሎች መስኮች የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማና መላውን ነዋሪ ተጠቃሚ ያደረጉ ናቸው። በግብርናው መስክ አርሶ አደሩ መስኖ ተጠቅሞ በበጋ ወራት በገበያ ተፈላጊ የሆኑና የተሻለ ዋጋ የሚያስገኙ ሰብሎችን እንዲያመርት እንዲሁም የራሱንና የቤተሰቡን ጉልበት በአግባቡ ልማት ላይ በማዋል ገቢውን እንዲያስድግ በተሰራ ስራ አበረታች ውጤት ከመመዝገቡ በተጨማሪ በአከባቢ አየር ለውጥ ምክንያት ወቅቱ፣ ስርጭቱና መጠኑ እየተዛባ ካለው የዝናብ ተፅዕኖ የሚያላቅቁ ስራዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል፡፡ በአነስተኛ ወጪና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በሁለት ዙር የመስኖ ልማት 180ሺህ 905 ሄክታር መሬት በስራስር፣ ቦሎቄ፣ ቦቆሎ፣ እና የጓሮ አትክልቶች በመሸፈን 26 ሚሊዮን 606ሺህ 342 ኩንታል ምርት ማምረት መቻሉን አስረድተዋል፡፡ ከክልሉ የሚመረተውን ቡና ጥራትና ደረጃ በማስጠበቅ በብዛት አምርቶ ለውጪ ገበያ በማቅረብ ሀገሪቱ የምታገኘውን የውጪ ምንዛሪ ለማሳደግና አምራች አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን 42 ሺህ 189 ቶን የታጠበና 40ሺህ 952 ቶን ያልታጠበ ቡና በግልና በማህበረት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ ተችሏል ብለዋል። በክልሉ በከተማና ገጠር 704 የውሃ ተቋማትን በመገንባት፣የማስፋፊያና የጥገና ስራ በማከናወን 1

ሀዋሳ ዪኒቨርስቲ ከ4 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎችን በቅድመና ድህረ ምረቃ ኘሮግራም ዛሬ አስመረቀ

አዋሳ ሐምሌ 06/2005 የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በ2006 የትምህርት ዘመን ለሚያካሄዳቸው ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ 1ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ከመንግስት የተመደበለት መሆኑን የዩኒቨርስቲው ፕሬዝደንት ገለጹ፡፡ ዩኒቨርስቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸው ከ4 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች በቅድመና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞ ዛሬ አስመርቋል፡፡ በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝደንት ዶክተር ዮሴፍ ማሞ እንደገለጹት ዩኒቨርስቲው በ2006 የትምህርት ዘመን በአራት ፕሮግራሞች ሰባት ውጤቶች ላይ በማተኮር 57 ዋና ዋና ተግባራትን ለማከናወንና 40 ፕሮጀክቶችን ለማስፈጸም 1ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ተመድቦለታል፡፡ ዩኒቨርስቲው የመማር ማስተማር፣ ምርምር፣ የህብረተስብ አገልግሎትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ከማካሄድ አኳያ በ2005 የበጀት አመት ከመንግስት በተመደበለት ከ975 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ መጠነ ሰፊ ስራዎችን ማከናወኑንም አስረድተዋል፡፡ እነዚህ ሰራዎች ዩኒቨርስቲው የቅበላ አቅሙን ለማሰደግና የትምህርት ጥራትን ለመጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጾኦ እንዳለው አመልክተው መንግስት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተነደፈው 70 በመቶ የቴክኖሎጂና ተፈጥሮ ሳይንስ መስክና 30 በመቶ ማህበራዊ ሳይንስ ሀገራዊ የተማሪ ቁጥር ምጣኔ ሙሉ በሙሉ መተግበሩን አስታውቀዋል፡፡ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የትምህረት ዘርፎች ተግባራዊ ያደረጉት አዱሱን ተማሪ ተኮር የሞጁለር የትምህርት አሰጣጥ ዘዴና ተከታታይ የተማሪዎችን ውጤት ምዘና ስርዓት አጠናክሮ በመቀጠል ከዚህ ቀደም ከትምህርታቸው ይሰናበቱ የነበሩ ተማሪዎች ቁጥር መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ በዘመኑ ለመማር ማስተማር የሚያግዙ የተለያዩ የትምህርት ግብኣቶችን የማሟላትና የማደራጀት ስራዎች መከናወናቸውን ዶክተር ዮሴፍ ጠቁ

‹‹ኔትዎርክ የለም››

ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ተግባራዊ ለማድረግ የአገሪቱ ባንኮች በግልና በኅብረት ሆነው እንቅስቃሴዎች እያደረጉ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ ስድስት የግል ባንኮች የኤቲኤም አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡ ከዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶች አንዱ በመሆን የሚጠቀሰው የኤቲኤም እዚህ እንደ አዲስ እንየው እንጂ በዓለም ላይ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ከ40 ዓመታት በላይ ሆኖታል፡፡ ሌሎች ዘመናዊ የምንላቸውን የባንክ የአገልግሎት ዓይነቶችም ገና በመግባት ላይ ናቸው ወይም ለማስገባት ዕቅድ ተይዟል፡፡ ለአገራችን አዳዲስ የምንላቸውን ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶች ለማግኘት ባንኮች ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ ቅርንጫፎቻቸውን በኔትዎርክ አስተሳስረዋል፡፡ በሞባይል ገንዘብ ለማዘዋወር የሚያስችለውን ቴክኖሎጂም ሊጀምሩ ነው፡፡ ከኤቲኤም ጀምሮ ወደፊት ተግባራዊ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችን ወደተግባር ለመለወጥ ደግሞ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የቴሌን ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡ አገልግሎቶቹ ከኔትዎርክ ጋር የሚያያዙ በመሆኑ የኔትዎርክ ችግር ካለ አገልግሎቱን መስጠት አይችልም፡፡ ሰሞኑን እንደታዘብነው ግን የኔትዎርክ ችግር በትንሽ ደረጃ የተጀመረውን ዘመናዊ የባንክ ሥራ እየፈተነው ነው፡፡ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ነው በሚባለው የኔትዎርክ ችግር የባንክ ደንበኞች ተገቢውን አገልግሎት እያገኘን አይደለም በማለት እያማረሩ ናቸው፡፡ ገንዘብ ለማስገባትና ለማስወጣት ብዙ እንግልት እየደረሰብን ነው የሚሉት የባንክ ደንበኞች በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ችግሩ በተደጋጋሚ መከሰቱን ይጠቁማሉ፡፡  ሰሞኑን በኔትዎርክ ችግር ምክንያት እየተጉላላን ነው ካሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች መካከል የአንድ ድርጅት ሠራተኛ ጨርቆስ አካባቢ በሚገኘው የኢት

የሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሐ ግብርን ለመከታተል ስድስት ባለሥልጣናት ኃላፊነት ወሰዱ

የዜጐችን የሰብዓዊ መብት ለማስከበር መንግሥት ነድፎታል የተባለውን የሦስት ዓመታት የድርጊት መርሐ ግብር በበላይነት የሚከታተል ብሔራዊ ኮሚቴ ተመሠረተ፡፡ ስድስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የኮሚቴው አባል በመሆን ኃላፊነት ወስደዋል፡፡ የድርጊት መርሐ ግብሩን በበላይነት ለመከታተል የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ የፍትሕ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው አምባዬ በመሆን የተመረጡ ሲሆን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ነጋ ፀጋዬ በምክትል ሰብሳቢነት ተመርጠዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አምባሳደር ጥሩነህ ዜና የብሔራዊ ኮሚቴው ጸሐፊ ሆነዋል፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሽመልስ ከማል፣ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሙሉጌታ ውለታው የኮሚቴው አባላት ሆነው የመከታተል ኃላፊነቱን ወስደዋል፡፡  ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብር በሚል ስያሜ መንግሥት ያዘጋጀው ሰነድ በሦስት ዓመታት ውስጥ የዜጐችን ሕገ መንግሥታዊ መብቶች በተሻለ ሁኔታ በማክበርና በማስከበር፣ በዚህ ረገድ የሚታይበትን ከፍተኛ ጉድለት ለመቅረፍ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡  በቅርቡ በፓርላማ የፀደቀው የድርጊት መርሐ ግብር ካካተታቸው ጉዳዮች መካከል የሕግ አስከባሪዎች ያላግባብ በተጠርጣሪዎች ላይ የሚፈጽሙት ድብደባ አንዱ ሲሆን፣ እንደዚህ ዓይነት ተግባር በሚፈጽሙ የፖሊስ አባላት ላይ ጥብቅ የሆነ ዕርምጃ ለመውሰድ በዕቅዱ ተካቷል፡፡  ከዚህ በተጨማሪ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በእስር በመያዝ ረዥም ጊዜ የሚፈጅ ምርመራ ማድረግ በሕግ አስከባሪው ዘንድ የሚታይ ጉድለት መሆኑን በመግለጽ፣ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ ለማድረግ የጊዜ ገ

የቡና ቦርድ በድጋሚ ሊቋቋም ነው

መንግሥት ከዓመታት ቆይታ በኋላ በድጋሚ የቡና ቦርድ ለማቋቋም ወሰነ፡፡ በአሁኑ ወቅት የቡና ዘርፍ ራሱን የቻለ ባለቤት ስለሌለው ችግር ውስጥ ገብቷል በሚል ምክንያት በድጋሚ የቡና ቦርድ እንዲቋቋም መወሰኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ እስካሁን መንግሥት ስትራቴጂ የሚላቸውን ዘርፎች የሚከታተል፣ ችግራቸውን የሚፈታና የሚቆጣጠር ኤጀንሲ ሲያቋቁም ቆይቷል፡፡ በእስካሁኑ ሒደትም የአበባና አትክልት፣ የጨርቃ ጨርቅና ጋርመንት፣ የቆዳና የቆዳ ውጤቶችን ዘርፍ የሚከታተሉ ተቋማት መመሥረታቸው ይታወቃል፡፡  በዚሁ ቅርጽ አገሪቱ የምትታወቅበትና ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሪ የሚያስገባው ቡና ራሱን የቻለ ቦርድ እንዲቋቋምለት ሐሳቡ ቀርቦ በመንግሥት ተቀባይነት አግኝቷል፡፡  በአሁኑ ወቅት ቡና ከምርት ጀምሮ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እስኪደርስ ድረስ በግብርና ሚኒስቴር ባለቤትነት ይካሄዳል፡፡ ከምርት ገበያ እስከ ኤክስፖርት ድረስ ያለው ሒደት በንግድ ሚኒስቴር ባለቤትነት ይከናወናል፡፡ ቡና በንግድ ሚኒስቴር ውስጥ እንደማንኛውም የግብርና ምርት የሚታይ በመሆኑና ትኩረት ያልተሰጠው በመሆኑ፣ በግብይት ሒደት ከፍተኛ ችግሮች መፈጠራቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የሚደረገው እንቅስቃሴ ዘገምተኛ መሆኑን በዘርፉ ውስጥ የተሰማሩ ሰዎች ይናገራሉ፡፡  እነዚህ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት፣ የቦርዱ መቋቋም ቢዘገይም አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም፡፡ በንጉሡ ዘመን የቡና ቦርድ የሚባል ተቋም ነበር፡፡ በወታደራዊው መንግሥት የሥልጣን ዘመንም የቡናና ሻይ ሚኒስቴር በመባል ነበር፡፡ ኢሕአዴግ አገሪቱን ሲቆጣጠር የቡና ዘርፍ ትኩረት እያጣ መምጣቱን የሚናገሩት የቡና ነጋዴዎች፣ ዘርፉ ከጊዜ ወደ ጊዜ ማደግ ሲገባው እየቀጨጨ መምጣቱን ይናገራሉ፡፡  በአዲሱ ዓመት የቡና

በደቡብ ክልል የፕሬዚዳንትነትን ቦታ ለሲዳማ ብሄር ተወላጆች ክፍት በማድረግ ኢህኣዴግ የሲዳማን ክልል ጥያቄ በማፈን ላይ ነው

ሲዳማ ባለፉት 20 ኣመታት ህዝባዊ የፖለቲካ ጥያቄዎችን በተመለከተ ፖለቲካዊ ኣንድነትን ከመቼውም ጊዜ በላይ ያሳየው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንትነትን ቦታ በሌላው የደቡብ ብሄር በተነጠቀበት ወቅት ብቻ ነው ማለት ይቻላል። ይሄውም የቀደሞውን የክልሉ ፕሬዚዳንት ኣቶ ኣባተ ኪሾን በሙሲና ተከሰው ከስልጣን ላይ መነሳታቸውን ተከትሎ ወደ ክልሉ ፕሬዚዳንትነት የመጡት የኣሁን የኣገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የክልሉ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ጊዜ ብቻ ነው፤ ሲዳማ ህዝቡም ሆነ ህዝቡ የመረጣቸው የፖለቲካ መሪዎች በኣንድ ኣፍ የተናገሩት እና ለሁሉም ጥቅም መከበር ኣብረው የሰሩት። ከጊዜ ውጭ በተለይ የሲዳማ ተወላጆች የክልሉን ፕሬዚዳንትነትን በያዟቸው ወቅቶች በሙሉ ማለት ይቻላል በሲዳማ ህዝብ ጥቅሞች ላይ ኣንድ ኣይነት ኣቋም ተይዞ ኣልታየም። በተለይ የሲዳማን የክልል ጥያቄን በተመለከት የህዝቡ ፍላጎት እና የፖለቲካ ኣመራሮቹ ፍላጎት ለየቅል ሆነው ታይተዋል። ለኣብነት ያህል ኣቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የክልሉ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ጊዜ በወቅቱ የሲዳማ ዞን ዋና ኣስተዳዳሪ በነበሩት በኣቶ ገርመው ጋርጄ የምመራው የሲዳማ የፖለቲካ ኣመራር ለሲዳማ የክልል መንግስት ያስፈልገዋል በማለት ከከተማ እስከ ገጠር ድረስ ካድሬዎቹን በማሰማራት ህዝብ የማሳመን ስራ ስርቷል። የክልል ጥያቄ በህዝብ ውስጥ ስር እንዲሰድ እና በኣንድነት ሆ ! ብሎ እንድደግፋቸው ኣድርገዋል። በጊዜ የሲዳማ ህዝብም በኣመራሮች ለህዝባቸው መቆርቆር ከመደሰቱ እና ከመኩራቱ በላይ ለጥያቄው መሳካት በነብሱን ገብረውለታል። ይህ ጊዜ የሲዳማ ኣባቶች እና እናቶች በልጆቻቸው የኮሩበት፤ ምራቃቸውን ተፍተው የመረቋቸው ጊዜ እንደነበር የምታወስ ነው። በእርግጥም በወቅቱ በያዙት እና በፈጸሙት ጀግንነት መ

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ተጀመረ የክልሉን ርዕስ መስተዳደር ሹመት ጽድቋል

ከሃዋሳ በደረሰን ዜና መሰረት የቀደሞውን የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ ተክተው ኣቶ    ደሴ ዳልኬ  ተሹመዋል። የኣቶ ደሴ ዳልኬ መሾም ሲዳማ በደቡብ ክልል መንግስት ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ሚና ትልቅነት የሚያሳይ እና በክልሉ ያለው የፖለቲካ መሪነት ቀጣይነት ያረጋገጠ ነው ተብለዋል። ሲዳማን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ተዋቅሮ የነበሩት ብሄርና ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ወደውም ሆነ ሳይወዱ በኣንድ ክልል ከተጠቃለሉ ጊዜ ጀምሮ ሲዳማ የክልሉን ፖለቲካ በበላይነት መምራቱን ቀጥሎበታል። እስከ ኣሁን የደቡብ ክልልን ከመሩት እና በመምራት ካሉት ኣራት ርዕስ መስተዳደሮች መካከል ሶስቱ ከሲዳማ ናቸው። ኣቶ ደሴ ዳልኬ ባለፉት ኣስራ ሁለት ኣመታት በሲዳማ ዞን ውስጥ በተለያዩ የስራ ሃላፊነቶች ላይ የሰሩ እና ላለፉት ሶስት ዓመታት የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው የቆዩ ናቸው። የኣቶ ደሴ ዳልኬ ወደ ደቡብ ክልል ተመልሰው መምጣት ለሲዳማ ያለው እድምታ ምን እንደሆነ ለጊዜው ግልጽ ባይሆንም በሲዳማ ዘንድ የተደበላለው ስሜት ፈጥሯል። ኣቶ ደሴ ዳልኬ በሲዳማ ህዝብ ዘንድ በየጊዜው እየተነሳ የቆየውን የሲዳማ ክልል ጥያቄን በተመለከተ የሚኖራቸውን ኣቋም ከዚህ በፊት ከነበሩት የክልሉ መሪዎች የተለየ እንደማይሆን የተገመተ ሲሆን ለክልል ጥያቄው ኣዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ የሚያደርጉ ከሆነ የሲዳማ ህዝብ ድጋፊ እና ፍቅር ሊያገኑ ይችላሉ ተብሏል።

አቶ ደሴ ዳልኬ የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳድር ሆኑ

ሃዋሳ ሐምሌ 06/2005 የክልሉ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ መደበኛ ጉባኤ አቶ ደሴ ዳልኬን የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት ርእሰ መስተዳድር አድርጎ መረጠ፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ ከቀድሞው ርእስ መስተዳድር ከአቶ ሽፈራው ሽጉጤ የክልሉን መንግስት ቁልፍ በመረከብ በይፋ ስራ ጀምረዋል፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ደሴ ዳልኬ እንዳስገነዘቡት ክልሉ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ማእከል በመሆኑ ለእኩል የልማት ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ትኩረት ሰጥተው ይሰራሉ፡፡ መላ የክልሉን ሕዝብ በአንድነት ለማጠናከር የተጀመሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ የሲዳማ ብሔር ተወላጅ ሲሆኑ የትምህርት ዝግጅታቸው በስነ ህይወት ሳይንስ የመጀመሪያና በለውጥ አመራር ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸውና ከወረዳ ጀምሮ እስከ ፌዴራል በተለያየ የሃላፊነት እርከን ያገለገሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ የቀድሞው ርእስ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ባለፉት ስምንት አመታት በክልሉ ልማትና መልካም አስተዳደር እንደዲሰፍ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የክልሉ ምክር ቤት አባላትና ድርጅቱ እውቅና ሰጥቷቸዋል፡፡ http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=9613&K=1

Hawassa University graduation ceremony 2005

Hawassa University to hold a graduation ceremony for 2005 E.C. graduates on July 13 & 14,2013 consecutively @ Main Campus.  " Congratulation to all graduating students"

መልካም ሳምንት ለመላው ሲዳማ _ኣዱኛ ዱሞ ሃኖ

ኣዱኝ ዱሞ ሃኖ