ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በመጪው ጥቅምት 2006 ዓ.ም. በሐዋሳ በሚካሄደው የመጀመርያው የኃይሌ ገብረሥላሴ ማራቶን አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው 340 ግራም ወርቅ እንደሚሸልም አስታወቀ፡፡ ታላቁ ሩጫ ከአሜሪካው ሞሬ ማውንቴን ስፖርት ጋር በመተባበር ጥቅምት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. በሐዋሳ ከተማ ስለሚያካሂደው የማራቶን ውድድር በሰጠው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ ትልቁን ሽልማት ለአሸናፊ ወንድና ሴት አትሌቶች ያቀረበ መሆኑንና አሸናፊዎቹ እያንዳንዳቸው 340 ግራም ወርቅ (12 አውንስ) ወርቅ ተሸላሚ ይሆናሉ ብሏል፡፡ ‹‹ኃይሌ ገብረሥላሴ ማራቶን›› ተብሎ በየዓመቱ የሚካሄደው ውድድር የመጀመርያው ሕዝባዊ ማራቶን እንደሚሆንና ከዋናው ማራቶን በተጨማሪ ግማሽ ማራቶን፣ የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫና የልጆች ሩጫንም ያካትታል፡፡ ይህን ልዩ የሩጫ ዝግጅት አሸናፊዎች ብቻ ሳይሆኑ 12 ዕድለኛ ተሳታፊዎችም በልዩ ዕጣ እያንዳንዳቸው አንድ አውንስ (28 ግራም) ወርቅ ይሸለማሉ፡፡ ተባባሪ አዘጋጁ ሞሬ በሐዋሳው ውድድር ከመላው ዓለም ተሳታፊዎች እንዲመጡ ለማድረግ በበርሊን፣ ቺካጎ፣ ኒው ዮርክ ማራቶኖች የቅስቀሳ ሥራ ማድረጉም እስካሁን ባለው ምዝገባ ከ20 አገሮች ከ100 በላይ ተሳታፊዎች መመዝገባቸውንም አስታውቋል፡፡ እንደመግለጫው፣ ሐዋሳ ከተማ ባሏት ሰፋፊ መንገዶችና መልክአ ምድራዊ አቀማመጧ ዳገት ቁልቁለት ያልበዛባትና ለጣማነት ስላላት ከባሕር ወለል በላይ ያላት አቀማመጥ ለማራቶን ተመራጭ አድርጓታል፡፡ በተያያዘ ዜና የ2006 ዓ.ም. ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ10 ኪሎ ሜትር ዓለም አቀፍ ውድድር ምዝገባ ሰኔ 22 ቀን 2005 ዓ.ም. መጠናቀቁን አዘጋጁ ክፍል አስታውቋል፡፡ ተሳታፊዎች ትጥቃቸውን የሚረከቡት ውድድሩ አራት ቀን ሲቀረው ከኅዳር 11-14/2006 ዓ.ም. በኤግ
It's about Sidaama!