ሃዋሳ ግንቦት 23/2005 በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ በተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ከ5 ሺህ በላይ ጎልማሶች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑን የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አዝመራ አመኑ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በወረዳው በሚገኙ ከ35 በሚበልጡ ትምህርት ቤቶችና ጊዜያዊ የማሰተማሪያ ስፍራዎች ማንበብና መጻፍ ለማይችሉ ጎልማሶች ትምህርት እየተሰጠ ነው። በወረዳው ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ጎልማሶችን በመለየትና ለ96 አመቻቾች የማስተማር ስነዘዴ ስልጠና በመስጠት 5 ሺህ 947 ጎልማሶች ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። በደረጃ አንድና ሁለት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ካሉት ጎልማሶች በተጨማሪ በቀበሌ አመራሮች በልማት ቡድኖችና በአንድ ለአምስት ትስስር አማካኝነት ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ጎልማሶች እየተለዩ መሆኑንና በአሁኑ ወቅት በወረዳው የጎልማሶች ትምህርት ሽፋን ከ56 በመቶ በላይ እንደደረሰ አቶ አዝመራ ተናግረዋል። የጎልማሶች ትምህርትን በተጠናከረ መልኩ ለማከናወን የወረዳው አስተዳደር ለአመቻቾች አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝና የማስተማሪያ መጽሀፍት ግዥ በመፈጸም ለሁሉም ጣቢያዎች እንዲዳረስ ማድረጉን አስታውቀዋል። በተጨማሪም አምስትና ስድስት ዓመት የሆናቸው 23 ሺህ 233 ህጻናት በ250 አመቻቾች የቅድመ መደበኛ ትምህርት በትምህርት ቤትና ከትምህርት ቤት ውጪ በተዘጋጁ የማስተማሪያ ስፍራዎች እየተማሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ልዩ ፍላጎት ያላቸውን አካል ጉዳተኞች በአካቶ የማስተማር ዘዴ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ 392 መስማትና ማየት የተሳናቸውና የተለያየ የአካል ጉዳት ያለባቸው ህጻናት በሰለጠኑ መምህራን እንዲማሩ መደረጉን አቶ አዝመራ ጠቁመዋል። የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ
የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል