አዋሳ ሚያዚያ 22/2005 የሲዳምኛን ቋንቋ፣ ባህልና ታሪክ ለማሳደግ ከ31 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ ፕሮግራሞች መዘጋጀታቸውን የዞኑ ባህል፣ ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ገለጸ፡፡ የመምሪያው ሀላፊ አቶ ወርቅነህ ፍላቴ ሰሞኑን እንደገለጹት ከፕሮግራሞቹ መካከል ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ከስምንት ወራት በፊት የተጀመረው የብሄረሰቡን ቋንቋ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ሶፍት ዌር የማዘጋጀት ስራ ይገኝበታል፡፡ ሲዳምኛ በዞኑ የስራና የትምህርት ቋንቋ እንደመሆኑ በዞኑ በሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወጥና ደረጃውን የጠበቀ ቋንቋ መጠቀም ለዕደገቱ ከፍተኛ አሰተዋጾኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡ ይህም እስከ ወረዳ በተዘረጋው የመንግስት መዋቅር ስር በሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከአንድ ወር በኋላ በኮምፒተሮቻቸው የመጫን ስራ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡ ለሰፍት ዌሩ ስራ የወጣውን ጨረታ አሸንፎ ስራውን ያከናወነው ድርጅት በላቤት አቶ ታደለ አሰፋ በበኩላቸው የሶፍት ዌር ስራው 30 ከሚበልጡ የውጪ ሀገራት ቋንቋዎች ሶፍት ዌር በመቀመር መሰራቱን ተናግረዋል፡፡ ከሀገር ውስጥ ሁኔታ ጋር ለማስተዋወቅና ለማጣጣም በሲዳምኛ ቋንቋ ከተዘጋጁ የተለያዩ የህትመት ውጤቶች ከ100 ሺህ በላይ ቃላት መሰባሰባቸውን አመልከተው ሙያዊ ቃላትን ጨምሮ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ቃላት በድግግሞሽ ሶፍት ዌር ውስጥ ሊገባ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ ይህንን ስራ ለመገምገምና ለእርምት ከተሳተፉት ባለሙያዎች አቶ አሰፋ ሙቁራ፣ አቶ ተፈራ ሌዳሞ እንዲሁም በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሲዳምኛ ቋንቋ ዲፓርትመንት መምህር አቶ ማቴዎስ ወልደጊዮርጊስ በሰጡት አስተያየት ሶፍት ዌሩ ቋንቋው በማህበራዊ ፣ በኢኮኖሚና በፓለቲካ ጉዳዮች የተሟላ እንደሚያደርገው ጠቁመው ቋንቋ ለስነጹሁፍ እድገት ከ
It's about Sidaama!