የሲዳማ ብሔረሰብ በደቡብ ክልል ከሚገኙ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ነው። ሲዳማ የሚለው ቃል ለሕዝቡና ለመሬቱ የተሰጠ ስያሜ ሲሆን « ሲዳንቾ » የሚለው ቃል ደግሞ ለሁለቱም ፆታዎች ሲዳማነታቸውን የሚገልጽ ነው፡፡ ብሔረሰቡ በዋናነት ከሚኖርበት አካባቢ ውጪ በኦሮሚያ ክልል በባሌ፣ በጉጂ፣ በምዕራብ አርሲ ዞኖች እና በክልሉ በወላይታና በጌዴኦ ዞኖች ውስጥ ይኖራል። የብሔረሰቡ ዋና የኢኮኖሚ መሠረት እርሻና ከብት እርባታ ሲሆን፤ አነስተኛ የዕደ ጥበብ እና የንግድ እንቅስቃሴዎች በተወሰኑ የማኅበረሰቡ ክፍሎች ይከናወናሉ። በብሔረሰቡ እንሰት፣ ቡና፣ በርበሬ፣ ጐመን፣ ሽንኩርት፣ በቆሎ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ጤፍ፣ አጃ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ቦሎቄ፣ አቦካዶ፣ አናናስ፣ ማንጐ፣ ሙዝ፣ ፓፓያ፣ አብሽ፣ ኮረሪማ፣ በሶብላ፣ ድንች፣ ስኳር ድንች፣ ቦይና፣ ሸንኮራ አገዳና ጫትን በዋናነት ያመርታል። የብሔረሰቡ ቋንቋ « ሲዳምኛ » ሲሆን ከምሥራቅ ኩሻዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ ይመደባል። ከካምባታ፣ ከጠምባሮ፣ ከኦሮሞ፣ ከሀላባ ከቀቤና እና ከጌዴኦ ቋንቋዎች ጋር ይቀራረባል። ብሔረሰቡ ከአፍ መፍቻ ቋንቋው በተጨማሪ አማርኛ፣ ኦሮምኛ እና ወላይትኛን ኩታ ገጠም በሆኑ አካባቢዎች ይጠቀማል። የሲዳማ ብሔረሰብ የራሱ የሆነ ባህላዊ አስተዳደርና የፍትህ ሥርዓቶች ያሉት ሲሆን፤ አጥፊዎች የሚዳኙበት « ሴራ » የተባለ ሕግ አላቸው። የባህላዊ አስተዳደሩ የበላይ አካል « ወማ » ( ንጉሥ ) ነው። ሥልጣኑም በዙር የሚተላለፍ በመሆኑ እያንዳንዱ ጐሣ የራሱ ወማ አለው። በብሔረሰቡ በርካታ የጋብቻ ሥርዓቶች ያሉት ሲሆን « ሁጫቶ » በቤተሰብ ፈቃድ የተመሠረተ፣ « አዱልሻ » ማስኮብለል፣ « ዲራ » ጠለፋ፣ « ራጌ » የውርስ ጋብቻ እና « አዳዋና » ሴቆ - ቱጋ ሴት ልጅ ዕድ
It's about Sidaama!