አዲስ አበባ፣ጥቅምት 21 ፣2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የስኳር ምርትን ባለፈው ዓመት ወደ ውጭ መላክ ይጀመራል ተብሎ የነበረ ቢሆንም የስኳር ፕሮጀክቶቹ በታሰበላቸው ፍጥነት እየሄዱ እንዳልሆነ ተገለጸ። የስኳር ኮርፖሬሽን እንደሚለው ለፕሮጀክቶቹ መጓተት ዋነኛው ምክንያት የአቅም ውስንነት ነው። ቀደምሲልየማስፋፊያስራእየተሳራባቸውየነበሩየስኳርፋብሪካዎችንና ነባርየስኳርፋብሪካዎችንበመጠቀምካለፈውዓመትጀምሮየስኳርምርትለውጭገበያለማቅረብታቅዶየነበረሲሆን፥እንደታቀደውግንማድረግአተቻለም። የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ልዩ አማካሪ አቶ አስፋው ዲንጋሞ እንዳሉት ፥ የኮንትራክተሮችም ሆነ የአማካሪዎች አቅም ውስንነት ፣ የገንዘብ እጥረት ፣ በበቂ የሰው ኃይል አለመደራጀት ፣ ለፕሮጀክቶቹ መጓተት በምክንያትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው። ከፕሮጀክቶቹ ግዝፈትና ውስብስብነት ጋር በተያያዘም ፥ የስኳር ኮርፖሬሽንም ቢሆን የፕሮጀክት አመራርና አስተዳደር ድክመት እንደነበረበትና፥ በአሁን ወቅት ግን ችግሮቹ በመለየታቸው በያዝነው ዓመት ፕሮጀክቶቹን በአዲስ መልክ ለማፋጠንና ለማጠናቀቅ ርብርብ በመደረግ ላይ መሆኑንም ነው ያስረዱት። ኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክቶቹን በአዲስ መልክ ለመምራት እንዲያስችለውም ፥ ባለፉት ሶስስት ወራት ቁልፍ ችግሬ ነበር ላለው የአቅም ውስንነት ትኩረት ሰጥቶ ሰርቷል ፥ እየሰራም ነው። የሰው ኃይሉን አቅም ለማጎልበትም በውጭ ሃገራት ጭምር በመላክ የተለያዩ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እያደረገ ነው። የከሰም ስኳር ፋብሪካ በጣም ከዘገዩት ውስጥ አንዱ ሲሆን ፥ የፋብሪካ ግንባታውንም በዚህ ዓመት በአብዛኛው በማጠናቀቅ በቀጣዩ ዓመት ወደ ማምረት ስራ እንዲገባ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ፥ የወልቃይት፣የበለስና ስድስት ፋብሪካዎች የሚገነቡበት የደ
It's about Sidaama!