Skip to main content

ዕውቀት እንረዳለን
አራተኛ ክፍል እያለሁ የሂሳብ መጽሐፍ ለአራት ነበር የሚታደለን፡፡ ታድያ የቤት ሥራ የተሰጠ ቀንመጽሐፉን ለመውሰድ ተረኞች ያልነበርነው ሦስታችን የቤት ሥራውን ስንገለብጥ ከተማሪው ሁሉወደ ኋላ እንቀር ነበር፡፡ ሕፃናት ስለ ነበርን፣ ከዚያም የተሻለ ስላላየን መጽሐፍን ለአራት ለአምስትመውሰድ የዓለም ሥርዓት መስሎን ነበር ያደግነው፡፡ የመጽሐፍ ኮንደሚኒየም አትሉም፡፡
የሚገርመው ነገር ይህ አሠራር በሁለተኛ ደረጃም ሆነ በኮሌጅ ደረጃ ሳይሻሻል ነው እኛ ትምህርት«ጨርሰን» የወጣነው፡፡ በተለይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ እያለሁ እንድናነብየሚሰጠንን መጽሐፍ ቤተ መጻሕፍት ሄዶ ማግኘት አስቸጋሪ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሌላ ሰው ቀድሞያወጣውና ወረፋ ያዙ እንባላለን፡፡ ወረፋው ሳይደርሰን ፈተናው ቀድሞ ይደርሳል፡፡ አንዳንድ ጊዜደግሞ ከነ አካቴው መጽሐፉ አይኖርም፡፡ ምነው? ስንል «መምህሩ አውጥቶታል» እንባላለን፡፡ ሌላጊዜ ደግሞ «በኮርስ አውት ላይኑ» ላይ ያለው የመረጃ መጻሕፍት ዝርዝር ከሌላ የተገለበጠ ይሆንናቤተ መጻሕፍቱ እንኳን ሊኖረው ሰምቷቸውም አያውቅ፡፡
 እንዲህ እኛ መጽሐፍ ብርቅ ሆኖብን አድገን በኋላ ገዝታችሁ አንብቡ ስንባል ውቃቤ ሊቀርበንአልቻለም፡፡ እኛ በመጽሐፍ መከራ እንጂ መች ደስታ አይተን እናውቅና፡፡ ታች ክፍል እያለንመጽሐፉን እንድንጠቀምበትና እንድንፈተፍተው የሚፈቅድልን አልነበረም፡፡ ወላጆቻችንምአነበባችሁ? ከሚሉን ይልቅ « መጽሐፉ ይቀደድና የሚከፍልልህ አታገኝም» ነበር የሚሉን፡፡
እንዲያውም አምስተኛ ክፍል አንድ ጓደኛችን ትዝ ይለኛል፡፡ በዓመቱ መጀመርያ ለሦስትም ይሁንለአምስት ከሌሎች ጋር መጽሐፍ ወስዶ ነበር፡፡ አንድ ሦስቱ መጽሐፍ ለግል ይሰጥ ነበር መሰል፡፡ታድያ ለግል የሚሰጠውን መጽሐፍ የቤት ሥራውን ከሌሎች ተማሪዎች ሲገለብጥ እናየው ነበር፡፡
በዓመቱ መጨረሻ መጽሐፍ ልንመልስ ስንሰለፍ የርሱ መጽሐፍ አበባ እንደመሰለ ነበር፡፡ አንዳንድጓደኞቻችን ተናደዱበት፡፡ «አንተ በኛ መጽሐፍ የምትሠራው የራስህ እንዳይበላሽ ነው አይደልእያሉ አፋጠጡት፡፡ እርሱ ግን «ማርያምን» እያለ ይምል ይገዘት ነበር፡፡ ግን ማን ይመነው፡፡ሲጨንቀውና ከጓደኞቹ ሊቃቃር ሲሆን ጊዜ እውነቱን ነገረን፡፡ «እማዬ ስለቆለፈችበት ነው» አለን፡፡አንድ ላይ «ለምን አልነው፡፡ «ከተበላሸ የምከፍለው የለኝም ብላ ቆለፈችበት»፡፡ አለን አንገቱንአቀርቅሮ፡፡
ምን ያድርግ ለእርሱ እናት ዋናው ነገር ልጃቸው ያመጣው መጽሐፍ ሳይበላሽና ተጨማሪ ወጭ ሳያስ ከትል መመለሱ እንጂ መጠቀሙ አይደለም፡፡ ልጅ እንዳያጠፋ እንጂ እያጠፋም ቢሆን እንዲሠራማን ይፈቅድለታል?፡፡ ትምህርት ቤቱም ቢሆን የሚያስጠነቅቀን እንድንጠቀምበት ሳይሆንእንዳናበላሸው ነው፡፡ እኛም የምንጨነቀው ላለማበላሸት እንጂ ለማንበብ አልነበረም፡፡
ይህንን ሁሉ ያመጣው የኢኮኖሚና የአስተሳሰብ ድህነት ነው፡፡ ሀገሪቱ ለመጽሐፍ የምመድበው በቂበጀት የለኝም፤ ስለዚህ ያላችሁን አብቃቁ ትላለች፡፡ [እዚህ ላይ አንድ የመንገድ ላይ ትዝታላውጋችሁ፡፡ አራት ልጆች ወደ አንድ ከተማ ለሥራ ጉዳይ ሲሄዱ አንድ የምሳ መመገቢያ ከተማይደርሳሉ፡፡ እዚያ ከተማ ሲደርሱ ከግራ ከቀኝ የመጡት የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች ምግብቤቶችን ሁሉ ከአፍ እስከ ገደብ ጢም አድርገዋቸዋል፡፡
ያልተጨናነቀ ቦታ ሲፈልጉ ሁለት ለግላጋ ሕፃናት ቦታ እናሳያችሁ ብለው በተለምዶ «ማዘር ቤት»የሚባል ቤት ውስጥ ወሰዷቸው፡፡ እናት ምግብ ሠሪ፣ ልጅ አስተናጋጅ ሆነው አገኟቸው፡፡ ምግብአዘዙ፡፡ አንዱ ቀይ ወጥ፣ አንዱ አልጫ፣ አንዱ ቅቅል፣ አንዱ ደግሞ ጥብስ፡፡ ልጅቱ ትእዛዝ ተቀብላከመሄዷ እናትዬዋ ወገባቸውን በመቀነት ታጥቀው መጡ፡፡ «እኔ አበራሽ አራት ዓይነት ወጥአልሠራም፤ ተስማሙና አንድ አድርጋችሁ እዘዙ» አሏቸው፡፡
ልጆቹም እየሳቁም፣ እየተገረሙም በቀይ ወጡ ጸኑ፡፡ ጥቂት ጊዜ ወስደው በትልቅ ትሪ ከአራት እንጀራጋር አመጡላቸው፡፡ በወጣት አበላል ላፍ ላፍ አደረጉና ቀና ሲሉ እንጀራው ከወጡ በልጦ አገኙት፡፡«ወጥ አስጨምሪልን» አሏት ልጅቱን፡፡ ገባች ወደ ጓዳ፡፡ አሁንም እናት ወገባቸውን ይዘው መጡ፡፡አሁን ቀጥ ብለው ወደ ትሪው ነው የሄዱት፡፡ እጃቸውን ሰደዱና በወጥ የራሰውን እንጀራ በጣታቸውእየፈተፈቱ «ምነው አበራሽ፣ ይሄ ወጥ አይደለም? የነካካውን ብሉ፡፡ ወጥ የሚጣፍጠውሲያብቃቁት ነው» እያሉ ፈተፈቱላቸው፡፡ ወይ እጅ መታጠብ፤ ሦስተኛ ክፍል ቀረ፡፡]
ይሄው መመርያ ነበር የሀገሪቱም መመርያ «አብቃቁት» የሚል፡፡

ሁለተኛው ደግሞ የአስተሳሰብ ድህነት የፈጠረብን ነው፡፡ ወላጆችም፣ መምህራኑም፣ የትምህርትአስተዳ ደሩም እጥረቱን እንደ አርባ ቀን ዕድል ተቀብለውት ያለ መፍትሔ ይቀመጣሉ፡፡ የመጽሐፍርዳታ ለመሰ ብሰብ፣ የቀድሞ ተማሪዎችን አስተባብሮ አብያተ መጻሕፍትን ለማጠናከር፣ የገቢማሰባሰቢያ መንገድ ተልሞ የመጻሕፍትን ቁጥር ለመጨመር ሲጥር የሚታይ አልነበረም፡፡
በተለይማ በዩኒቨርሲቲዎቻችን ውስጥ 2000 ዓምን ኮርስ 1965 ዓም መጽሐፍ መማር እንደነውር አይታይም ነበር፡፡ በውጭ ሀገር ካሉት መጽሐፍ ተርፏቸው መጣያ ካጡት ተቋማት ጋርበመነጋገር ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮች ነበሩ፡፡ ግን ምን ያደርጋል ውጭ ሀገር ተምረው የሚመጡትየዩኒቨርሲቲ አመራሮችና መምህራን የስኮላር ሺፑን ያህል አላሳሰባቸውም፡፡ አንዳንዱ የኮሌጅ ቤተመጻሕፍት «ቤተ መዛግብት» እስከመሆን የደረሰውም በዚህ ምክንያት ነበር፡፡ ለዐቅመ ኮሌጅያልደረሱ ተማሪዎች ደግሞ «በውሻ እራት ውሻ ቆሞባት» እንደ ሚባለው ያቺኑ ያለችውን መጽሐፍእየገነጠሉና እየሰረቁ፣ በላይዋ ላይ እየጻፉና እያሠመሩ ደብዛዋን ያጠፏታል፡፡
ኮሌጆቻችን ከሕዝብ ርቀው፣ ንጽሕ ጠብቀው የሚኖሩ ናቸው፡፡ ምሁራኑም «ዝጉሐውያንባሕታውያን» ናቸው፡፡ ኮሌጆቹን ሕዝቡ ምን እንደሚሠሩና ምን እንደሚጠቅሙም እንዲያውቅአይደረግም፡፡ በመን ግሥት በጀት እንጂ በሕዝብ ድጋፍ አይቋቋሙም፡፡ ሕዝቡ የኔ ናቸው፡፡ልደግፋቸው ይገባል እንዲላቸው አይፈልጉም፡፡ አንድም ቀን ከአካባቢያቸው ማኅበረሰብ ጋርተዋውቀው አያውቁም፡፡ በዚህም ምክንያት ከሕዝብ በስጦታ፣ በውርስ፣ በበጀት ድጋፍ፣ በርዳታ፣በገጽታ ግንባታና በአመራር ሊያገኙ የሚችሉትን ድጋፍ አላገኙም፡፡
ምሁራኑም ለአካዳሚያዊ ክበቡ እንጂ ለሕዝብ የተገለጡ አይደሉም፡፡ የሚጽፉት በእንግሊዝኛ፣የሚያሳ ትሙት በጆርናሎች፣ የሚከራከሩት በክፍል ውስጥ በመሆኑ ሕዝቡ በዙርያቸው እንጂአብሯቸው አይደ ለም፡፡ አንድ የዩኒቨርሲቲ ምሁር ሞተ ከሚሉት አንድ የዕድር ዳኛ ሞተ ቢሉትሕዝቡ አብዝቶ ያዝናል፡፡ የማን ሞት እንደሚጎዳው የሚያውቀው እርሱ ነውና፡፡
እንዲህ ሆነን ግን እስከ መቼ? መቼም ሮም በአንድ ቀን አልተሠራችምና ችግሩን ሁሉ በአንድ ጊዜላንቀርፈው እንችል ይሆናል፡፡ ግን ለመቅረፍ መጀመር አለብን፡፡ « ! ጨለማን ከመውቀስአንድ ሻማ ማብራት ይበልጣል» እንዳለው ኮንፊሽየስ ያልሆነበትን ምክንያት ብቻ እያነሣን ከምናትትእስኪ መለወጡን ከራሳችን እንጀምረው፡፡ በተለይ በውጭ ካለው ዳያስጶራ፡፡
በአሜሪካና በአውሮፓ በየትምህርት ቤቱና ኮሌጆቹ ዓመቱ ሲጠናቀቅ መጻሕፍቱ ይቀየራሉ፡፡ አዳዲስእትሞች ይመጣሉ፡፡ ያለፉት እትሞች ወይ በርካሽ ይሸጣሉ ያለበለዚያም ደግሞ በነጻ ይሰጣሉ፤ከባሰም ወደ «ድጌ ቤት» (Recycle house) ይላካሉ፡፡
እናም እስኪ ምናለበት የዕውቀት ርዳታ ለሀገራችን ብንጀምር፡፡ በምን መንገድ አትሉኝም፡፡በየአካባቢያችን ከሚገኙ ትምህርት ቤቶችና ኮሌጆች በርካሽ የምናገኛቸውን መጻሕፍት እንሰብስብ፡፡በአንዳንድ ኮሌጆች እንዲያውም አፍሪካውያን ተማሪዎች መግለጫና ካርቶን እያስቀመጡ በነጻከሚሰጡ ተማሪዎች ሲሰበስቡ አይቻለሁ፡፡ በምዕራቡ ዓለም አንድን ነገር ለብዙ ጊዜ ማስቀመጥእዳው የቦታ ጥበት ነውና በቶሎ እንዲ ወገድ ይመከራል፡፡ እኛም ይህንን ባህል እንጠቀም፡፡መጻሕፍቱን እንሰበስብ፡፡
እያንዳንዱ የውጭ ነዋሪም ለራሱ ቃል ይግባ፡፡ ወደ ኢትዮጵያ በሄደ ቁጥር ቢያንስ ሦስት መጽሐፍይዞ ለመሄድና በአካባቢው ለሚገኝ በመጽሐፉ ለመጠቀም ለሚችል ትምህርት ቤት ለመስጠት፡፡ሌላው ቢቀር በአካባቢያችን ለሚማሩ ወጣቶች እንስጣቸው፡፡ በሕዝብ ቤተ መጻሕፍትእናስቀምጣቸው፡፡ ለሠፈራችን ጎበዝ ተማሪዎች እንሸልማቸው፡፡ አያሌ ተማሪዎችን አስፈትኖመልካም ውጤት ላመጣ ትምህርት ቤት ዳያስጶራው መጻሕፍት ይሸልም፡፡
ቢያንስ በየዓመቱ ወደ አሥር  የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ከውጭ ይመጣሉ፡፡እያንዳን ዳቸው ሦስት መጽሐፍ ቢይዙ፤ በዓመት ሠላሳ  መጽሐፍ ወደ ሀገር ይገባል ማለት ነው፡፡በዐሥር ዓመት ስናስበው ደግሞ 300,000 መጽሐፍ ይሆናል፡፡ ከዚህ በላይ ምን የዕውቀት ርዳታአለ፡ ሀገሪቱስ ይህንን ያህል በጀት ለመጽሐፍ መመደብ ትችላለች ብላችሁ ነው?
ትምህርት ቤቶች ላይ ካልሠራን ስለ ዴሞክራሲና ሰብአዊ መብት፣ ስለ ሥልጣኔና ዕድገት ማውራቱቅዠት ይሆናል፡፡ ዕውቀት አጠር ሆኖ ያደገን ትውልድ ሥልጣኔ አጠር አትሁን ማለት ያልተወለደንልጅ እንደማሳደግ ይቆጠራል፡፡
እስኪ በቤታችሁ ግደግዳ ላይ፣ ወይም በፍሪጃችሁ በር ላይ «ዕውቀት እንረዳለን» ብላችሁ ለጥፉ፡፡ለሚጠይቋችሁ አስረዱ፡፡ በፌስ ቡካችሁ ላይ ለጥፉ፣ በቢሯችሁ ጠረጲዛ ላይ ጻፉ፡፡ በመኪኖቻችሁላይ እንደ ጌጥ ስቀሉ፡፡ ሀገር የሚለወጠው በዕውቀት ነው፡፡ ለውጥ የሚጀመረው ደግሞ ከትምህርትቤት፡፡
እስኪ ቃል እንግባ፡፡
ሽሮ እናስመጣለን፤ በርበሬ እናስልካለን፣ እኛም በተራችን ዕውቀት እንረዳለን፡፡
ኦክላንድ፣ ካሊፎርንያ

Comments

Popular Posts

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል

Sidama: the Luwa and the Anga Culture and their Social Implications

By Wolassa Kumo 1. Introduction In my previous articles, I mentioned the Sidama grand social constitution Seera, and various sub constitutions which derive from this grand constitution. We have also seen that all social constitutions or Seera in Sidama were based on the Sidama moral code of halale, the true way of life. In this socio-cultural and socio-political system, the role of the elders was very important. Elders were bestowed with the power of enforcing the Seera and referring the recalcitrant to Magano or God if he/she refuses to abide by the Seera. The power of elders in the Sidama society was not based on a simple age count as is the case in most modern societies. The Sidama elder is more the product of various social processes through which he passes than the product of a simple aging. For a person to become a recognised elder with authority in Sidama, he has to become a Cimeessa (respected elder with authority) or Cimeeyye for many respected elders. There are three importa