ከአስር ዓመታት በፊት “ሲዳማ ክልል ሁና ትደራጅ” የሚል ጥያቄ በማቅረባቸው በአንድ ቀን ውስጥ ከ60 በላይ የሆኑ የአዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በአጋዚ ጦር በግፍ ተጨፈጨፉ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ለአካል ጉዳቶች ተዳረጉ፤ በርካቶች ታሰሩ። ከሰባት ዓመታት በፊት ደግሞ - በምርጫ 97 ማግሥት – “ድምፃችን ይከበር” በማለታቸው እስካሁን ቁጥራቸው በትክክል የማይታወቅ የአዋሳ ወጣቶች ተገደሉ፤ በርካታ ወጣቶችና አዛውንት ታሰሩ፣ ተደበደቡ፣ ተጋዙ። ዛሬም አዋሳ በውጥረት ውስጥ ነች። የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ ሠራዊት እንደለመደው የአዋሳን እና የአካባቢው ነዋሪዎች ሊገድል፣ ሊያቆስል፣ ሊያስር ዘምቷል። ከአዋሳ ወጣ ብላ በምትገኘው አለታ ጭኮ የመለስ ዜናዊ ፓሊሶች ነዋሪዎችን ገድለዋል፤ በርካቶችን አቁስለዋል። ነዋሪዎችም በፓሊሶች ለደረሰባቸው ጥቃት በወሰዱት የመከላከል እርምጃ አንድ ፓሊስ ሕይወቱን አጥቷል። የሚሰማቸው ጆሮ አላገኙም እንጂ ሕዝብን ከሕዝብ በማጣላት ሙያ የተካኑት የመለስ ካድሬዎች “አዋሳ ከተማ ወደ ፌደራል ትጠቃለል ያሉት ወላይታዎች ናቸው” እያሉ በማስወራት ላይ ናቸው። መለስ ዜናዊ የፈጠረው ዘርን ብቻ መሠረት ያደረገው “ፌደራሊዝም” በማር የተለወሰ መርዝ መሆኑ ባለፉት ሃያ ዓመታት በተግባር ያየነው ጉዳይ ነው። የመለስ ዜናዊ የውሸት ፌደራሊዝም ከሁሉም የአገራችን ክፍሎች በባሰ የተሳለቀበት “የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት” በሚባለው የአገራችን ክፍል ነው። አዋሳ ደግሞ የዚህ የአቅጣጫ ስያሜ የተሰጠው “መንግሥት” መቀመጫ ናት። አዋሳ እና እሷ የምትወክለው “የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት” የመለስ ዜናዊ ፌደራሊዝም አስከፊ ገጽታ ማሳያዎች ናቸው። በመለስ ዜናዊ ፌደራሊዝም ምክንያት ውቧ አዋሳ የግጭቶች
It's about Sidaama!