የእናቶችንና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ታደሰ አነቦ ባለፉት ወራት የእናቶችን ሞት ለመቀነስ በተደረገው እንቅስቃሴ ለ2 ሺህ 985 እናቶች የቅድመ ወሊድና የድህረ ወሊድ ምርመራ እንዳደረገላቸውም ተናግረዋል፡፡ 14 ሺህ 49ዐ እናቶች የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን አብራርተው ቁጥራቸው በተጨማሪም እናቶች በባለሙያ የተደገፈ የወሊድ አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡በአንፃሩ የህፃናትን ሞት ለመቀነስ በተደረገው ርብርብ 3 ሺህ 383 ህፃናት የተለያዩ በሽታዎችን የሚከላከል ክትባት ማግኘታቸው መለሰ ሱኩሌ ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ ዘግቧል፡፡ ምንጭ: http://www.smm.gov.et/_Text/16MegTextN304.html
It's about Sidaama!