የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ትናንት ማምሻውን ተጠናቀቀ |
ሃዋሳ, የካቲት 21 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - የደቡብ ክልል ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ከ183 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት በማጽደቅ፣ አራት ዳኞችን ከሀላፊነታቸው በማንሳትና የአንድ የምክር ቤት አባል ያለመከሰስ መብት በማንሳት ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል፡፡ ጉባኤው በትናንት ውሎው ባለፉት ስድስት ወራት በክልሉ በተከናውኑ በትምህርት፣ በመንገድ፣ በጤናና ግብር አሰባሰብ ላይ በመወያየት የስድስት ወራት የክልሉን መንግስት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አጽድቋል። ምክር ቤቱ በበጀት ዓመቱ በቀጣይ በ15 ወረዳዎች ለሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ፣ በ10 ወረዳዎች አዲስ ለሚጀመሩ ፕሮጀክቶች፣ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለግብርናና ለክልል ቢሮዎች ለመደበኛና ለካፒታል በጀት ማሟያና ለመጠባበቂያ 183 ሚሊዮን 869 ሺህ 652 ብር ተጨማሪ በጀት አጽድቋል። ጉባኤው የተሰጣቸውን የዳኝነት ስልጣን ተገን በማድረግ በግለሰቦች ላይ በደል ፈጽመዋል የተባሉትን የአርባምንጭ አካባቢ ጋማ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ስንታየሁ ለማ፣ በጌድዮ ዞን የቡሌ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ፍላሳ ቡርቃ፣ የቦዲቲ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ፋንታ ቤርቦና የከፋ ዞን ጠሎ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ አደመ አርጋጎ ከኃላፊነታቸው በማንሳት ጉዳያቸው በህግ እንዲታይ ወስኗል። በሌላ በኩል ደግሞ አቶ ሙሉጌታ አጎን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ ሲሾም 24 አዲስ የወረዳ፣ የዞንና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት አጽድቋል። ምክር ቤቱ ትናንት ማምሻውን ሲጠናቀቅ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሽብቁ ማጋኔ በክልሉ ጸረ ሙስና ኮሚሽን በቀረበ ጥያቄ መሰረት ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የተደረገ ሲሆን ግለሰቡ የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅና ከንቲባ በነበሩበት ወቅት ያለአግባብ ስልጣንን በመገልገልና ከመሬት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ተጠርጣሪ በመሆናቸው ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ተደርጓል። እንዲሁም ወደ ፌዴራል መስሪያ ቤቶች በዕድገትና በዝውውር በሄዱት የትራንስፖርት፣ የባህል፣ ቱሪዝምና የአርብቶ አደር ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊዎች ምትክ አዲስ የቢሮ ኃላፊዎች ሹመት ተሰጥቷል። |
የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡ የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡ ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ
Comments
Post a Comment