የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሶሻል አንትሮፖሎጂ ፕሮግራም በሁለተኛ ድግሪ ደረጃ ሊከፍት ነው አዋሳ, ታህሳስ 13 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በብሄር ብሄረሰቦች ልማት ላይ ያተኮረ የሶሻል አንትሮፖሎጂ የትምህርት ፕሮግራም በሁለተኛ ድግሪ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመክፈት መዘጋጀቱን ገለጸ፡፡ የፕሮግራሙ መከፈት ለሀገሪቱ ህዝቦች ባህልና ቋንቋ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጾኦ እንዳለው የደቡብ ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ለማ ገዙሜ ገልጸዋል፡፡ ለፕሮግራሙ የተዘጋጀውን ስርዓተ ትምህርት ለመገምገም ከአሜሪካ የመጡና የሀገር ውስጥ ከፍተኛ ባለሙያዎች ትናንት ለግማሽ ቀን ባካሄዱት አውደ ጥናት ላይ የዩኒቨርሰቲው ፕሬዜደንት ዶክተር ዮሴፍ ማሞ እንደገለጹት አንዳንድ ቋንቋዎችና ባህሎች ሳይታወቁ የሚጠፉበት ሁኔታ እንዳለ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ ፕሮግራሙ ይህንን ችግር ከመቅረፍ ባሻገር የክልሉና የሀገሪቱን ብሄር ብሄረሰበችን ባህል ፣ ቋንቋ ፣ ወግ ፣ ታሪክና ዕድገት በማጥናት ፣ በመንከባከብና በማልማት ጠብቆ ለማቆየት ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥር አስታውቀዋል፡፡ በክልሉ ዋና ከተማ የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመጪው የካቲት 2004 ጀምሮ የሚከፍተው ፕሮግራም በተለይ በደቡብ የሚገኙትን ከ56 በላይ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቋንቋዎች ፣ባህሎች ሀይማኖቶች ፣ወጎችና ታሪካዊ እሴቶች በዘላቂነት ለማልማት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርስቲው የክልሉን የሰው ሃይል አቅም ከመገንባት ባሸገር ፖሊሲዎችንና ውሳኔዎችን ለማስተዋወቅ ከክልሉ መንግስትና የብሄረሰቦች ምክር ቤት ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡ የክልሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ለማ ገዙሜ በበኩላቸው ዩኒቨርስቲው በሁለተኛ ድግሪ ደረጃ የሚከ
የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል