ከቻይና የመጣ የልኡካን ቡድን በሀዋሳ ከተማ የተቋቋመውን የኢንዱሰትሪ መንደር ጎበኘ፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከቻይና ቾንቺን ግዛት ለመጣው የልኡካን ቡድን እንደገለጹት የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦቸና ህዝቦች መኖሪያ የሆነው የደቡብ ክልል በኢንዱሰትሪ፣ ግብርናና አገልግሎት ተቋማት መሳተፍ ለሚፈልጉ ባለሃብቶች ዕምቅ ሃብት ይገኝበታል፡፡ በክልሉ 22 የሪፎረም ከተሞች የመሰረተ ልማት አገልገሎት የተሟላላቸው የኢንዱሰትሪ መንደሮች መዘጋጀታቸውን ገልጸው በኢንዱስትሪ ዘርፍ መስራት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡ በክልሉ ካለው ምቹ ሁኔታ በመታገዝ ብዛት ያላቸው ባለሃብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን አፍስሰው እየሰሩ መሆኑን ገልጸው በክልሉ በማንኛውም መሰክ መሰማራት ለሚፈልጉ የቻይና ባለሃብቶችን ለመቀበል የክልሉ መንግስት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከቻይና የቾንቺን ግዛት የመጡት የልዑካን ቡድን ተወካይ የክልሉ መንግስት ላደረገላቸው አቀባበል አመስግነው የቻይናው ሊፋን ኢንዱስትሪ ፓርክ በሀዋሳ የመኪና አካላት ማምረቻና መገጣጠሚያ መንደር ለማቋቋም የተለያየ ስራ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የቾንቺን ግዛት በርካታ ኢንዱስትሪ የሚገኙበት መሆኑ
የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል