ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ‹‹ሁሉም›› በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው ሁለተኛው የሐዋሳ ኢንተርናሽናል ግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ኬንያዊው አትሌት ኪፕሊሞ ኪሙታይ በአገሩ ልጅ የተያዘውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፏል፡፡ በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ የኦሜድላ አትሌት ሲሳይ መአሶ አሸናፊ ሆናለች፡፡ የዘንድሮው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ‹‹ሁሉም›› በሚል ቃል የተዘጋጀው የእናቶችንና ሕፃናትን ሞት ለመቀነስና ለማስቀረት የሚያስችሉ መልዕክቶች እንዲተላለፉበት በሚል ሲሆን፣ በውድድሩ ከአትሌቶች ውጪ ከአራት ሺሕ በላይ በሩጫው ተሳትፈዋል፡፡ ውድድሩን የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ፣ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴና ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም አስጀምረውታል፡፡ በአትሌቶች መካከል በተደረገው 21 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ኬንያዊው ኪፕሊሞ ኪሙታይ ርቀቱን 1 ሰዓት 03 ደቂቃ 10 ሰኮንድ በሆነ ጊዜ ሲያጠናቅቅም፣ ይህም ባለፈው ዓመት በሌላው ኬንያዊ ዊልስ ቼሮት 1 ሰዓት 03 ደቂቃ 13 ሰኮንድ ተይዞ የቆየውን በ03 ሰኮንድ በማሻሻል አዲስ ክብረወሰን አሻሽሏል፡፡ በሴቶች መካከል በተደረገው የኦሜድላዋ አትሌት ሲሳይ መአሶ በ1 ሰዓት ከ16 ደቂቃ 41 ሰኮንድ አጠናቃ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች፡፡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለሁለቱም አትሌቶች የ10 ሺሕ ብር ሽልማት ሲሰጥ፣ ኬንያዊው ኪፕሊሞ ከሙታይ ለክብረወሰኑ ተጨማሪ የ3 ሺሕ ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡
የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል