በይርጋለም ከተማ ልዩ ስሙ አቦሶ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትናንት ምሽት 5 ሰአት ከ 8 ደቂቃ ላይ የከተሰተው። የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር እስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበበት መሆኑን በአዲስ አበባዩኒቨርስቲ የጂኦፊዚክስ ስፔስ ሳይንስ አስትሮኖሚ ኢኒስቲትዩት ተመራማሪ ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ተናግረዋል። በሌላ በኩል በሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳም ትናንት ምሽቱን ተመሳሳይ የመሬት መንቅጥቀጥ አደጋደርሷል። የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዴ ገቢባ ለኢዜአ እንደተናገሩት በወረዳው በሚገኙ 17 ቀበሌዎችላለፉት 10 ቀናት በተወሰነ የሰዓት ልዩነት በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ቆይቷል፡፡ ትናንት ከምሽቱ 5 ሰዓት ከ 10 ደቂቃ ላይ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የወረዳውአስተዳደር ጽህፈት ቤትን ጨምሮ ከ 100 የሚበልጡ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ፈርሰዋል። ጉዳትየደረሳበችው ሁለት ግለሰቦችም በይርጋለምና ቦካሶ ጤና ጣቢያ ህክምና እያገኙ ሲሆን 10 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ግምት ያለውንብረትም ወድሟል።
It's about Sidaama!