የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሃዋሳ ከተማ ተከበረአዲስ አበባ፣ህዳር 29 2003 (ሬዲዮ ፋና) አምስተኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች 
ቀን በአል በዛሬውዕለት በተለያዩ ክልሎችበድምቀት ተከበረ። በዓሉ የተከበረው
" የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች እጅ ለእጅ ተያይዘንየአገራችንን ህዳሴ ወደ 
ማይቀለበስት ደረጃ እናደርሳለን" በሚል መሪ ቃል ነው።

በአሉትናንት በተለይ በሃዋሳ ከተማ ሲከበር በበአሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙትየፌዴሬሽን
ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ካሳ ተክለብርሃን  የኢትዮጵያ የፌዴራሊዝም ስርአት 
በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ውጤታማ በመሆን ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። 

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በበኩላቸው ድህነትን ታግለን ማሸነፍ
እንደሚገባ አስታውቀዋል።

በበአሉ ላይ የተገኙ የብሄር ብሄረሰብ ተወካዮች ፌዴራላዊ ስርአቱ ተጠቃሚ እያደረገ ያለው
ብሄርብሄረሰቦችንና ህዝቦችን መሆኑን ጠቅሰው ህገ መንግስቱን በመጠበቅ ድህነትን ለመዋጋት
እንደሚረባረቡ አረጋግጠዋል።

በተያያዘምየብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን የሀገራችን ህዝቦች በመከባበር ላይ የተመሰረተ
አንድነታቸውን በማጠናከር ኢትዮጵያንመካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ የገቡትን
ቃል ዳግም የሚያድሱበት እንደሆነ የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ተናግረዋል።

ምክትልርዕሰ መስተዳደሩ አቶ አወል ወግሪስ ለሬዲዮ ፋና እንዳሉት ቀኑ ህዝቦች ያገኟቸውን
ህገ መንግስታዊ መብቶች በመጠቀም ልማትንለማፋጠንም ቃል የሚገቡበት ነው።

ለህዝቦች ራስን በራስ ማስተዳደር እንዲሁም በራስ ቋንቋ መማር፣ መስራትና መዳኘት መሰረት
ለሆነው ለዚሁ ቀን ከፍተኛ ስፍራ በክልሉ ህዝብ እንደሚሰጠው ገልጸዋል።

በተተመሳሳይ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦችን እኩልነትን ለማረጋገጥ የተከፈለውን
መስዋዕትነት በመጠበቅ ለሀገራችን ቀጣይ እድገት በጋራ መሰለፍ እንዳለብን  የትግራይክልል
ርእሰ መስተዳድር ተናግረዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ አቶ አባይ ወልዱ ዛሬ በመቀሌ  በተከበረው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና 
ህዝቦች ቀን ላይ እንዳሉት  ባለፉት ዓመታት የተገኙ ድሎችን በመጠበቅና አንድነታችንን  
በማጠናከር ድህነትን ለማጥፋት ጠንክረን መስራት አለብን ብለዋል።

መንግስት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፅድቆ  እንቅስቃሴ ማድረግ መጀመሩን
ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ እቅዱን ተግባራዊለማድረግና የሀገሪቱን ህዳሴ ለማረጋገጥ
መረባረብ እንዳለብን አሳስበዋል።

በበዓሉ ላይ የከተማው ነዋሪዎች፣ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ በከተማው የሚገኙ 
የ1ኛና ሁለተኛደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም የፖሊስ አባላት
ተገኝተዋል።

አምስተኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል ዛሬ በድሬደዋ ከተማ በሰላማዊ ሰልፍና
በተለያዩ ዝግጅቶች በታላቅ ድምቀት ሲከበር ውሏል።

በዓሉ በርካታ የድሬደዋ ሕዝብ በተገኘበት በድሬደዋ ስታዲዮም ነው የተከበረው።

በበአሉ ላይ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች፣የመከላከያ ሰራዊት አባላት
ወታደራዊሰልፍ፣ የስፖርትና ልዩ ልዩ ትርኢቶችን አቅርበዋል።

የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባዔ ወይዘሮ ቢፍቱ መሀመድ በዓሉን ስናከብር 
እየተመዘገበያለውን ሁለንተናዊ ልማት ለማስቀጠል ቃል በመግባት ሊሆን ይገባዋል ብለዋል።

በሌላበኩል በዛሬው ዕለት እየተከበረ ያለው የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን የሀገራችንን
አንድነት ለማጠናከር ሚናው ከፍተኛእንደሆነ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሰራተኞች ገልፀዋል።

ሰራተኞቹቀኑን ትናንት ከሰዓት በብሄራዊ ቲያትር አዳራሽ አክብረዋል።

በዚሁወቅት እንዳሉት በዓሉ የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦችን አንድነት ከማጠናከር 
ባሻገር የባህልና እሴት ልውውጥ እንዲኖርየሚያደርግ ነው።

ለብሄሮችብሄረሰቦችና ህዝቦች መብት መረጋገጥም ሆነ ለቀኑ መከበር መሰረት የሆነውን
የሀገራችን ህገ መንግስት ሁሉም በንቃት ሊጠብቀውእንደሚገባም አሳስበዋል።
No comments