አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እውቁ የኬንያ አትሌት ፖል ቴርጋት የኢትዮጵያ ታዳጊ ወጣቶች የኦሎምፒክ ውድድርን ለመታደም ሀዋሳ ከተማ ገብቷል፡፡ አትሌት ፖል ቴርጋት በሲዳማ ክልል አዘጋጂነት ከግንቦት 21 እስከ ሰኔ 4/2014 ዓ.ም ድረስ የሚካሄደውን 1ኛውን የኢትዮጵያ ታዳጊ ወጣቶች የኦሎምፒክ ውድድርን በክብር እንግድነት ለመታደም ነው ሀዋሳ ከተማ የገባው፡፡ በተጨማሪም የአፍሪካ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ አቶ አህመድ ጋሽም፣ የብሩንዲ ኦሎምፒክ ፕሬዚዳንትና የአፍርካ ኦሎምፒክ ሥራ አስፈፃሚ፣ የኬንያ ኦሎምፒክ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ዞን 5 ዋና ጸሐፊ፣ ዶክተር ቶኒ የደቡብ ሱዳን የኦሎምክ ፕሬዝዳንት፣ አቶ ልዑል ፍሰሃ የኤርትራ ኦሎምፒክ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ዞን 05 ዓቃቤ ንዋይ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም ሀዋሳ ገብተዋል። በተመሳሳይ የኦሎምፒክ ውድድሩን ለመታደም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፌጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ሀዋሳ ከተማ መግባታቸው ታውቋል፡፡ እንግዶቹ ሀዋሳ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሲዳማ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንትና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ ባራሳ፥ የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ ከኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ጋር በመሆን አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።። የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ታዳጊ ወጣቶች የኦሎምፒክ ውድድር በነገው ዕለት በሲዳማ ክልል አዘጋጅነት በሀዋሳ ከተማ ይጀመራል።
በሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልሎች አጎራባች አከባቢዎች የሚከሰቱትን ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያስችላል የተባለለት የሰላም ኮንፌራንስ በሐዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ ሰምተናል
ሰሞኑን በሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልሎች አጎራባች አንዳንድ ቀበሌያት ተከስተው በነበረው ግጭቶች በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ የሚታወሰ ሲሆን፤ ባለፉት ጥቅት ቀናት ይህንን በተመለከተ በአከባቢው ሰላለው አጠቃላይ የጸጥታ ሁኔታ እና በቀጣይነት ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ በመደረግ ላይ ባሉት ተግባራት ላይ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት አንዳንድ መረጃዎችን ለአንዳንድ የክልሉ የሚዲያ አውታሮች ስሰጡ ተመልክተናል። ባለፈው ሳምንት የተከሰተው እና በሰው ነፍስ እና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰው ግጭት በተለየ ሁኔታ እንደሚባለው በህዝቦች መካከል የተነሳ ሳይሆን፤ በኦሮሚያ ክልል የሚቀሳቀሱ የታጠቁ ሃይሎች በግልጽ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሲዳማ ልዩ ሃይል በኦሮሚያ መሰማራቱን በመቃዎም እና ለዚሁ የበቀል እርምጃ በሲዳማ ህዝብ ላይ እንደሚወስዱ በአደባባይ ካዛቱ በሃላ የፈጸሙት ነው። ይህንን የአሽባሪ ቡድን ተግባር በመጀመሪያ ደረጃ የሁለቱም ክልል መንግስታት በአደባባይ ማውገዝ እና ዳግም እንዳይከሰት ለማድረግ ቃል መግባት ሲገባቸው፤ ምንም ሳይሉ ማለፋቸው ብሎም በአጠቃላይ፤ ከመንግስትም ሆነ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በግዳዩ ላይ የተባለ ነገር አለመኖሩ በርካታ፣ በተለይ የሲዳማን ምሁራንን ማስቆጣቱ ይታወሳል። ያህም ሆነ ይህ ከቆይታ በሃላም ቢሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሰሞኑን በዳዬ ከተማ ውይይት ማድረጋቸው የተሰማ ሲሆን፤ በወይይቱም ላይ በአጎራባች አከባቢዎች በተደጋጋሚ የሚከሰቱትን ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፋታታ ያስችላል የተባለለት ሰነድ ላይ ውይይት መደረጉ እና ከስምምነት ላይ መደረሱ ታውቋል። ለወራንቻ ድረገጽ የደረሱ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ፤ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ አርሲ ዞን እና በሲዳማ ክልል የድንበር ሰላምን ለማስፈን የተዘጋ