Skip to main content

የሀዋሳ ከተማን የመጠጥ ውሃ እጥረት ለማቃለል በ20 ሚሊዮን ብር እየተካሄደ ያለው የማስፋፊያ ፕሮጀክት ከ90 በመቶ በላይ ተጠናቀቀ

አዲስአበባ፣ታህሳስ12 2003 (ሬዲዮፋና)የሀዋሳ ከተማን የመጠጥ ዉሃ እጥረት ለማቃለል በ20ሚሊዮን ብር 
እየተካሄደ ያለው የማስፋፊያ ፕሮጀክት ከ90 በመቶ በላይ መጠናቀቁን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ ።
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የጥልቅ መጠጥ ዉሃ ግንባታ ለማከናወን የሚያስችል ጥናት
መጠናቀቁም ተገልጧል ።
የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሽብቁ ማጋኔና ሌሎች የካቢኔ አባላት በወንዶ ገነት አካባቢ የሚገኘዉን የመጠጥ
ዉሃ ማስፋፊያ ግንባታ ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል ።
ከንቲባዉ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት በሃዋሳ ከተማ የኢንቨስትመንት መስፋፋትን ተከትሎ 
በከፍተኛ ደረጃ እያደገ የመጣዉን የመጠጥ ዉሃ ፍላጎት ለማርካት የተለያዩ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸዉ ።
ችግሩን ለማቃለል ከአለም ባንክ በተገኘ 16 ሚሊዮን ብር እና የከተማ አስተዳደር በመደበዉ 
የአራት ሚሊዮን ብር ወጪ የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት ስራ ከ90 በመቶ በላይ መከናወኑን አስረድተዋል።
ለከተማዋ ዘላቂ መፍትሄ ለማስገኘት ሃዌላ ወንዶና ጋራ ሊቀታ በተባሉ ስፍራዎች በሰከንድ
ከ200 እስከ 300 ሊትር ዉሃ መስጠት የሚያስችሉ የሁለት ጥልቅ የዉሃ ጉድጓደችን ቆፋሮ ለማካሄድ 
የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁን ገልጠዋል ።
በጥናቱ መሰረት ፕሮጀክቱ ለሃያ አመታት ለከተማዋ አስተማማኝ የመጠጥ ዉሀ ለማቅረብ የሚያስችል
መሆኑም ተገልጧል ።
የሃዋሳ ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ለጣ የታሞ በበኩላቸዉ 
በወንዶ ገነት አካባቢ በመገንባት ላይ ያለዉ የአምቦ የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት በቅርቡ አገልግሎት 
መስጠት ሲጀምር በሰከንድ 55 ሊትር ማምረት እንደሚቻል ተናግረዋል።
የፕሮጀክቱ አማካሪ መሃንዲስ አቶ ታከለ ፍሰሃ በበኩላቸዉ በአሁኑ ወቅት የዋናዉ ምንጭ የማጎልበት 
ስራና የ10 ኪሎ ሜትር የዉሃ መስመር ዝርጋታ መጠናቀቁንና የአንድ ነጥብ ሶስት ኪሎ ሜትር 
መስመር ዝርጋታና ፣ አንድ ሚሊዮን ሊትር ዉሃ የሚይዝ የዉሃ ማጠራቀሚያ ጋን ግንባታ 
በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልጠዋል።

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም
‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል አድርገው ይገልጻሉ፡፡ ዳርዳ…

የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ መልካም እድል ለሲዳማ ልጆች

New

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል።
ከዛሬ ጀምሮ በኢንተርኔት ድረ ገጽ www.nae.gov.et መመልከት እንደሚችሉ የሀገር አቀፈ ፈተናዎች ኤጀንሲ ለፋና በሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል።
የተማሪዎች ውጤት በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሚሰራጭ ሲሆን ፥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም እና የመሰናዶ መግቢያ ውጤትም በቀጣይ ሁለት ቀናት ይፋ እንደሚሆን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሄር ተናግረዋል።
በዘንድሮው አመት ፈተናውን የወሰዱ የመደበኛ ተማሪዎች ቁጥር 519,948 ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ 283,712 ወንድ እና 236, 236 ሴቶች ናቸው።
የዚህን ዓመት የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን ስንመለከትም ፥ 67 ነጥብ 23 በመቶ የሚሆኑ መደበኛ ተማሪዎች ከ2 ነጥብ በላይ አስመዝግበዋል።

ፈተናውን ከወሰዱ ተፈታኞች ውስጥ 1 ነጥብ 7 በመቶ የሚሆኑት 8 ሺህ 849 ተማሪዎች 4 ነጥብ ማምጣት የቻሉ ናቸው ተብሏል።
ከእነዚህም ውስጥ 6 ሺህ 441 የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ ሴቶች ደግሞ  የቀረውን 2 ሺህ 408 ቁጥር እንደሚይዙ ባህሩ ይድነቃቸው ዘግቧል።
http://www.fanabc.com/Story.aspx?ID=25767&K=

የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 23 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10ኛ ክፍል ማጠቃለያና የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ማለፊያ ነጥብ ውጤትን ነገ ይፋ እንደሚያደርግ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የዩኒቨርስቲ መግቢያና ወደ መሰናዶ ማለፊያ ነጥብን ለመወሰን  ፥ የዩኒቨርስቲዎችን ቀጣይ የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት መወሰኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው። በአጠቃላይ 548 ሺህ 138 ተማሪዎች የ10 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናውን ወስደው 70 በመቶዎቹ 2 ነጥብ እና ካዛ በላይ ውጤት ሲያስመዘግቡ ፥ በተመሳሳይም የ12ኛ ክፍልን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ከወሰዱት መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ተፈታኞች ከ350 ነጥብ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ቀደም ሲል  የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውሷል ። በነገው እለትም የሁለቱም ፈተናዎች የመቁረጫ ውጤት ይፋ ይደረጋል ተብሏል።